Hadiya Hossana Fc

Hadiya Hossana Fc ይህ ታማኙ የነብሮቹ ቤት ነው :: ድልና ድምቀት ለአምባሳዳራችን ⚪⚫🔴𝐇𝐎𝐊💪.
(1)

በክፉም በደጉም በከፍተኛ ሊግም ሆነ በፕሪምየር ሊጉ ለ11 ዓመታት ሙሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ፤ደስ አለኝ ደበረኝ ሳትል በታመኝነት ለክለብህ እና ለማልያው ያደረከውንና እያደረከው ያለውን ተጋድሎ መ...
22/07/2026

በክፉም በደጉም በከፍተኛ ሊግም ሆነ በፕሪምየር ሊጉ ለ11 ዓመታት ሙሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ፤ደስ አለኝ ደበረኝ ሳትል በታመኝነት ለክለብህ እና ለማልያው ያደረከውንና እያደረከው ያለውን ተጋድሎ መቼም አንረሳውም ። 💪

#ኑርልን
🐅
🐅
#አምባሰደራችን❤

ያልጨረስከውን ነገር ለገዘጠኞች ይፈ አታድርግ 👏የሀገራችን ዝውውር ግን ..!!!
21/07/2026

ያልጨረስከውን ነገር ለገዘጠኞች ይፈ አታድርግ 👏

የሀገራችን ዝውውር ግን ..!!!

  !የላቀ ምስጋና መልእክት ከዋና አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድያከበሩኝን ስላከበርኩ፣ ቦታ የሰጡኝ ላይ ስላልታበይኩ፣ ላመኑኝ ስለታመንኩ፣ የሚወዱኝን ስለምወድአልሀምዱሊላህ (ተመስገን) 🙏ወዳጆቼን ...
19/07/2026

!
የላቀ ምስጋና መልእክት ከዋና አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ
ያከበሩኝን ስላከበርኩ፣ ቦታ የሰጡኝ ላይ ስላልታበይኩ፣ ላመኑኝ ስለታመንኩ፣ የሚወዱኝን ስለምወድ
አልሀምዱሊላህ (ተመስገን) 🙏

ወዳጆቼን ስለምወድ ፣ሚስጥራቸውን ስለምጠብቅ፣ አለኝታ የሆኑኝን ስለማልረሳ፣ ሲወድቁ ጉድለታቸውን ስለማላጎላ፣ሳጠፋ ስለምፀፀት
አልሀምዱሊላህ (ተመስገን)🙏

ዝቅ ሲባልልኝን ልፈናጠጥ ስለማልል፣ አክብሮትን ስለምረዳ፣ ታላላቆቼንም ታናናሾቼንም ስለማከብር፣በደል ማንነቴን ስላልነጠቀኝ ፣መውደቅ ሰነፍ አድርጎኝ ስላልሄደ ፣ የሰው ዋጋ ስለገባኝ
አልሀምዱሊላህ (ተመስገን)🙏
የስንብት እና የላቀ ምስጋና መልእክት ከዋና አሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ
በሀዲያ ሆሳዕና ስፖርት ክለብ ውስጥ ላለፉት ሁለት ዓመታት በአሰልጣኝነት ሳገለግል ከቆየሁ በኋላ፣ አሁን ከክለቡ ጋር ያለኝን የስራ ውል በስምምነት አጠናቅቄ በይፋ መለያየቴን ለመግለጽ እወዳለሁ። ላለፉት ሁለት አመታት በሆሳዕና የነበረኝ ቆይታ በስራዬ ላይ ትልቅ ልምድ ያገኘሁበት፣ እጅግ አስደሳች እና ስኬታማ ጊዜ ነበር።
ለዚህም በቆይታዬ ሁሉ ከጎኔ ለነበሩት አካላት በሙሉ የከበረ እና የላቀ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ፦
1. ለክለቡ ፕሬዚዳንት ለአቶ ደነቀ እና ለቦርድ አባላት
የክለባችን ፕሬዚዳንት አቶ ደነቀ ክለቡን በትጋት በመምራት፣ ለስራችን መሳካት ካሳዩት ከፍተኛ ቁርጠኝነትና አርአያነት ያለው አመራር ጀርባ በመሆን ላደረጉልኝ ያልተገደበ ድጋፍና እምነት የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳቸው። እንዲሁም መላው የቦርድ አባላት ለስራችን ስኬታማነት አስፈላጊውን ሁሉ በማመቻቸት ለሰጣችሁኝ ሙሉ ክብር አመሰግናለሁ።
2. ለክለቡ ስራ አስኪያጅ ለአቶ አባተ
በየቀኑ በነበረን የስራ እንቅስቃሴ ውስጥ ያጋጠሙንን ፈተናዎች በጋራ እየፈታን፣ ለቡድኑ መረጋጋት እና ለስራችን መቃናት ላደረግከው ቀጣይነት ያለው ትልቅ አስተዋጽኦ እና ሙያዊ ድጋፍ ልዩ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
3. ለክለቡ የቡድን መሪ ለአቶ እስክንድር ደሳለኝ
ለቡድናችን ዝግጅት፣ ለስልጠናም ሆነ ለጨዋታዎች የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ማቴሪያሎችና ፋሲሊቲዎች (ሎጅስቲክስ፣ ካምፕ፣ ጉዞና መገልገያዎች) በማሟላት ረገድ ላደረግከው ከፍተኛ አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናዬ ይድረስህ። ሌሊት ከቀን በመልፋት ያለምንም እንግልት በብቃት ሁሉንም ነገር በማዘጋጀትህ፣ እንዲሁም በየጉዞዎቻችንና በካምፕ ቆይታችን ላሳየኸው ታላቅ ትጋትና ወንድማዊ ድጋፍ ልባዊ እና ልዩ ክብር አለኝ።
4. ለክለቡ ቴክኒክ ዳይሬክተር ለዶክተር ዘላለም
የክለቡን የቴክኒክ መዋቅር በመምራት፣ ከእኔ ጋር በነበረህ ቀጣይነት ያለው ሙያዊ ውይይት፣ ለታክቲክና እቅድ ስኬታማነት እንዲሁም ለታዳጊዎች እድገት ላበረከትከው የላቀ የቴክኒክ እገዛ ምስጋናዬ የላቀ ነው።
5. ለሀዲያ ቴሌቪዥን ስፖርት አዘጋጆችና ጋዜጠኞች በተለይም ለአቅራቢው ታሪኩ አበራ
ክለባችን የሚሰራቸውን ስራዎች፣ የምናደርጋቸውን ጨዋታዎች እና የቡድናችንን እንቅስቃሴ ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ፣ በሰፊው እና በሙያዊ ስነ-ምግባር ለሰራችሁት ድንቅ የሚዲያ ሽፋን፣ እንዲሁም ለሰጣችሁን ገንቢ ድጋፍ በራሴ እና በቡድኑ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
6. ለአሰልጣኞች ቡድን እና የህክምና ክፍል አባላት
ሌሊት ከቀን አብራችሁኝ በመልፋት፣ በታማኝነት እና በከፍተኛ የቡድን መንፈስ ለሰራችሁት ድንቅ ስራ ትልቅ ክብር አለኝ። ያለ እናንተ እገዛ ይህንን ጉዞ መጓዝ አይቻልም ነበር።
7. ለተጫዋቾቼ
በሜዳ ላይ እና ከሜዳ ውጪ ላሳያችሁት ታላቅ ስነ-ስርዓት፣ ለነበራችሁ የመስዋዕትነት መንፈስ እና እኔ የምፈልገውን የታክቲክ ሀሳብ በሜዳ ላይ ለመተግበር ላደረጋችሁት ተጋድሎ ሁሉ እጅግ ኮርቼባችኋለሁ። ወደፊትም በስራችሁ ትልቅ ደረጃ ላይ እንድትደርሱ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ።
8. ለሀዲያ ሆሳዕና አፍቃሪዎች እና ደጋፊዎች
ቡድናችን በሚያሸንፍበትም ሆነ በሚቸገርበት ወቅት በስፖርታዊ ጨዋነት መድረክ ላይ በመገኘት የሰጣችሁን ፍቅር እና የማያቋርጥ ድጋፍ መቼም ቢሆን አልረሳውም። እናንተ የክለቡ እውነተኛ የጀርባ አጥንት ናችሁ።
በመጨረሻም፣ ለሀዲያ ሆሳዕና ስፖርት ክለብ በምኞት ደረጃ ሳይሆን በተግባር የሚታይ ታላቅ ስኬት እና ብሩህ ተስፋን እየተመኘሁ፤ በክለቡ ስምምነቴን ጨርሼ ብለያይም ሁልጊዜም ለክለቡ መልካም አክባሪ ሆኜ እቀጥላለሁ።
አመሰግናለሁ!

ሰበር ዜና:- ክለባችን አድስ አሰልጣኝ ቀጥሯል!የሀዲያ ሆሳዕና ቦርድ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን የክለቡ ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ማረጋገጥ ችለናል። ከተጫዋችነት እ...
18/07/2026

ሰበር ዜና:- ክለባችን አድስ አሰልጣኝ ቀጥሯል!

የሀዲያ ሆሳዕና ቦርድ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን የክለቡ ቀጣዩ አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ማረጋገጥ ችለናል። ከተጫዋችነት እስከ አሰልጣኝነት ቅዱስ ጊዮርጊስን ያገለገሉት እና ዘንድሮ ክለቡን ከበርካታ ፈተናዎች ጋር በመታገል ለስኬት አብቅተው ያጠናቀቁት የቀድሞው የባህርዳር ከተማ ፣ መቻል ፣ አዳማ ከተማ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ጭምር ያገለገለው አሰልጣኙ በሁለት አመት ውል አዲሱ የሀዲያ ሆሳዕና አሰልጣኝ ማምሻውን ሆኗል።

መልካሙን እንመኛለን 👏
15/07/2026

መልካሙን እንመኛለን 👏

15/07/2026

Ka wosha
Hanqi ise!

ለኢትዮጵያ ዋንጫ እስከ መጨራሻ የተፋለሙ የቀድሞው የክለባችን ዋና አሰልጣኞች !Ayenne qed he'uda'e kaba agaakko.
10/07/2026

ለኢትዮጵያ ዋንጫ እስከ መጨራሻ የተፋለሙ የቀድሞው የክለባችን ዋና አሰልጣኞች !

Ayenne qed he'uda'e kaba agaakko.

ታርክ አይረሳውም !ለግላቸው ጥቅም ሳይመች ስቀር በግፍ የተሰናበተው የኛው  #ማንቾ ወልዋሎ አ.ዩንቨርስቲን የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ አድርጎታል። ከመንቾ መሰናበት የተጠቀመው ማን እንደሆነ ዩ...
09/07/2026

ታርክ አይረሳውም !

ለግላቸው ጥቅም ሳይመች ስቀር በግፍ የተሰናበተው የኛው #ማንቾ ወልዋሎ አ.ዩንቨርስቲን የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ አድርጎታል።

ከመንቾ መሰናበት የተጠቀመው ማን እንደሆነ ዩተጎደውስ ማን እንደሆነ በግልጥ ታይቷል ።

Xandoommoyyo.
Bal amadiisebe'e boge cawita .

መንቾ!🔥ወልዋሎ አዲግራት ዩ. የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
09/07/2026

መንቾ!🔥
ወልዋሎ አዲግራት ዩ. የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።

ተጠናቀቀ።12ኛ ደረጃ ይዘን አጠናቅቀናል
05/07/2026

ተጠናቀቀ።
12ኛ ደረጃ ይዘን አጠናቅቀናል

Address

Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya Hossana Fc posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category