Ąďåñė Mėłęśę AM

Ąďåñė Mėłęśę AM I am so in ❤love with the man who died on the cross✝️ in order to save👌 my soul! Jesus died for you!

08/05/2026

Tsega ahunim yichemerilih

05/12/2025
I agreed!!
18/08/2025

I agreed!!

ሰሞኑን እዚህ Facebook ላይ "በዚህ ሳምንት መጨረሻ እጣ የሚወጣለት ሰው አለ ተቀበል" የሚል የትንቢት 😊 post ተደጋጋሚ በማየቴ ነው ነገሩ የተከሰተው
እኔም በትዕዛዙ መሰረት ይሄንን መልዕክት ለ 50 ሰዎች ሼር አድርጌ ነበር😊😊።
እና እጣው ከደረሰኝ ብዬ Telebirr ላይ Ethio Lottery ብፍቅ ብፍቅ ፤ፍንክች ምንም የለም😂😊። ሊደርሰኝ አልቻለም ይኸው ሰኞም ገባ 😊😂።( አይ ስቀልድ ነው)

📍ወደዋናው ቁምነገር ስገባ ምን ለማለት ፈልጌ ነው ፤Social media ላይ scroll ባደረግን ቁጥር ይሄ ትንቢት ላንተ/ ላንቺ ነው የሚሉ የቪዲዮ መልዕክቶች በሙሉ ለ እኛ አይደሉም። ደግሞ ሳቢ ናቸው ይህንን ቪዲዮ እንዳታሳልፈው ይሉሀል ለ 10 ሰው ሼር አድርገው ይሉሀል።እውነተኛ የእግዚአብሔር መልዕከተኞች እንዳሉም አብዛኞቹ መልዕክቶች ደግሞ ከ እግዚአብሔር አይደሉም፤ጌታ ተናገረኝ በማለት እንደኔ እንዳትወዛገቡ ነው ።በተሸራረፈች ቪዲዮ መፅናናቱን ትተን ወደ እግዚአብሔር ቃል እውነት እንመለስ።

ማን ይሙት ቆይ አሁን በዚህ ወር መጨረሻ የትዳር በር ተከፈተ የሚል ባጋጣሚ ባይስ ፤አሜን ብል ይሆናል? 😊😊

I’m really tired of all this witchy, fortune-telling nonsense that keeps popping up everywhere on my Fyp page , and exhausting to see people chasing after that kind of foolishness instead of real truth.

16/07/2025

🚹ምን አይነት ትውልድና_ዘመን ነው?🚺
==========/////=========
✅ ድንግልናን ከማስወሰድ በላይ ስልክን መሰረቅ በጣም የሚያስቆጭበት ትውልድ

✅ ሴቶች ከHIV ይልቅ እርግዝናን የፈሩበት አስነዋሪ ትውልድ

✅ I Phone መያዝ ተምሮ ከመመረቅ በላይ የሚደሰትበት ትውልድ

✅ ሴቶች እምብርትንና ጡትን በአደባባይ እንደ ከተማ ህንፃ እዩኝ እዩኝ እያሉ ለዲያቢሎስ የተማረኩበት ትውልድ

✅ ፍቅር በዋጋ ሴክስ በነፃ የሆነበት አሳፋሪ ትውልድ

✅ እውነት ተዳፍኖ ውሸትና ክህደት እውነት መስሎ የታየበት አፀያፊ ዘመን

✅ ህዝቡ ከፈጣሪ ይልቅ አሸባሪ ፣ ገዳይና ሌባን የሚፈራበት አስቀያሚ ዘመን

✳ ገንዘብ ከቤተሰብና ከጉደኛ በላይ የተወደደበት ርካሽ ትውልድ

✳ በፍቅረኛ ላይ ሌላ ካልደረቡ "ፋራ" ተብሎ ሰውን
የሚሳደቡበት ትውልድ

✳ ሰው ሞልቶ ተርፎ ብቻን እንዲኖሩ ያስገደደ አሳዛኝ
ዘመን

✳ ለፍቅር መታመን ፣ ለፍቅር መሰደድ ፣ ለፍቅር መሰቃየትና መሞት እንደ ሞባይል game የተቆጠረበት ቅስም ሰባሪ ትውልድ

✳ ባልና ሚስት የማይተማመኑበት መሽቶ ላይነጋ የጨለመ ዘመን

✳ ወንዶች ሱሪን ዝቅ አድርጎ መታጠቅ ስልጣኔ መስሏቸው ለሰይጣን የሰገዱበት የተረገመ ትውልድ

✳ ሴቶች እምብርትንና ጡትን በአደባባይ እንደ ከተማ ህንፃ እዩኝ እዩኝ እያሉ ለዲያቢሎስ የተማረኩበት ትውልድ

✳ አለባበስ ታይቶ የሰውን ማንነት በአብረቅራቂ ነገርና በአይን ብቻ የሚገምት ትውልድ

🙏 ወደ ፈጣሪ ቦታ ሲከድ ስልክና ኤርፎን ይዞ የሚሄድ ትውልድ

14/07/2025

የኢየሱስ አማላጅነት በመጽሐፍ ቅዱስ

“ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”
— 1ኛ ዮሐንስ 2፥1

🔹ከላይ ባለው ጥቅስ ውስጥ ጠበቃ የምለውን ቃል እንመልከት ጠበቃ ማለት የሰውን መብት ለማስጠበቅ በፍርድ ቤት በሕግ መሠረት ቆሞ የሚከራከር ነው።
ስለዚህ የጠበቃ ሥራ ወንጀል የሰራውን ሰው ወክሎ የምከራከር ሰው ማለት ነው ስለዚህ ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችን እኛን ወክሎ ይከራከራል ማለት ነው ።

ይከራከራል ማለት እንደ ፍርድ ቤት ጠበቃ የሆነ ሙግት እንደገጠመው የምከራከር ሳይሆን በመስቀል በሰራው ሥራ የጠበቃ ስራው ዛሬም ሕያው ነው ማለት ነው።
መጽሐፍ ቅዱሳችን በግልጽ ኢየሱስ ጠበቃችን ነው እያለ ይነግረናል ስለዚህ ኢየሱስ ስለ ኃጢአታችን የጠበቃ ሥራ ይሰራል ማለት ነው።

ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?
³⁴ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

🔹ይህንን ሁለተኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንመልከት እግዚአብሔር የመረጣቸውን የምከስ የሚኮንን ማን ነው እያለ ይጠይቀናል? ከዚያ ሰውን የምያጸድቀው እግዚአብሔር ነው ይለናል ከዚያ የኢየሱስን ምልጃ ይነግረናል ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው የምያጸድቅ እግዚአብሔር በሆነበት ማን ነው ኮናኝ የምሆነው ሰለዚህ ኩነኔ ብመጣ እንኳን ጳውሎስ አማላጅ በአብ ቀኝ አለን ይላል ስለዚህ የኢየሱስ ምልጃ አሁን ባለበት በአብ ቀኝም የቀጠለ ነው ማለት ነው እንጂ በምድር ቆይታው ብቻ ያቆመ አይደለም ።

ዕብራውያን 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ስለ እነርሱም #ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።

🔹ከዚህ ጥቅስ እንደምንረዳው ኢየሱስ እንደ ብሉይ ክዳን ካህናቶች የእርሱ የክህነት ምልጃ በሞት የሚቆም እንዳልሆነ እና ከሞት ከመነሳቱ በኃላም የቀጠለ እንደሆነ ያስረዳናል ኢየሱስ ዛሬም ሕያው የሆነበት አንደኛው ምክንያት በእርሱ ለምያምኑት ሊያማልድ ነው።

— ኢሳይያስ 53፥12
“ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም #ማለደ።”

🔹በምድር በነበረ ጊዜ ስለ ኃጢአተኞች በመሞቱ እና ደሙን ለእነርሱ በማፍሰስ እንደ ማለደ ቅዱሱ መጽሐፋችን ይነግረናል ።

ሀሳቤን ስጠቀልለው የኢየሱስ ምልጃ በምድር ምልልሱ ብቻ ያበቃ ሳይሆን አሁን ባለበት በሰማይም የቀጠለ እንደሆነ እናያለን ።

🔹በምድር ቆይታቸው የማለዱ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱሳችን አሉ ግን የኢየሱስ ምልጃ ለየት ያለ እና ተወዳዳሪ የሌለው የሚያድርገው እና የእርሱ ምልጃ በምጠራበት ቦታ ሌሎች ምልጃዎች ምንም እና ከንቱዎች የሚሆኑበት ምክንያት እርሱ ለምልጃ ጸሎት ወይም ቃል ብቻ አይደለም ያዋጣው ደሙንም አፍስሶአል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ፈራጅ ብቻ ሳይሆን አማላጅም ነው።
የኢየሱስ ምልጃን ላለመቀበል በአዕምሮአችን ወደ ማን ይማልዳል እያልን የምንጠይቅበት ጉዳይ አይደለም በሥላሴ አምናለሁ ለምል ሰው እና ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ወደ ምድር እንደመጣ ለምያምን ሰው የኢየሱስን ምልጃ መቀበል አይከብደውም።

🔹ኢየሱስ አማላጅ ነው ስባል የጴንጤዎች ወይም የወንጌል አማኞች ትምህርት ወይም ስብከት ሳይሆን የመጽሐፍ ቅዱስ እና የሐዋርያቱ አስተምህሮ ነው።

10/04/2025

ዘጠናው ደቂቃ አልቆ ጭማሪ 7 ደቂቃ ተጨምሯል....የበርናባው የውጤት ማሳያ ስክሪን ላይ MAD 2 - 0 ARS ያሳያል.... በዚህ ውጤት ከተጠናቀቀ አርሰናል በደርሶ መልስ ውጤት ወደቀጣዩ ዙር የሚያልፍ ይሆናል....90+6 ላይ ማድሪድ ኮርና አግኝቶ ሲሻማ ቤሊንግሀም ቦክስ ውስጥ ይወድቃል.... ጨዋታው ቀጥሏል ኳሷን ቤን ኋይት በረጅሙ ጠልዞ ያወጣታል....ይቺ ኳስ ማርቴኔሊ እግርስር ትደርሳለች..... ማርቲኔሊ ለትሮሳርድ፣ ትሮሳርድ ለኦዴ፣ ኦዴ መልሶ ለማርቲኔሊ፣ ማርቲኔሊ በሚገርም አጨራረስ ኳስን ከመረብ አገናኘ......ግዙፉ ሳንቲያጎ በርናባው በአርሰናል ተጨዋቾችና ደጋፊዎች አበደ....( እዚህ ያሉ ደጋፊዎችም ወያላዉ ዝም በሚለው የወያላ ጭፈራቸው ጆሯችንን አደሙት)....... ፈረንሳዊው የመሀል ዳኛ ከVAR ዳኞች መልዕክት ይደርሰዋል.....ቤሊንግሀም ላይ ፋውል ተሰርቷል.... ዳኛው ሂዶ ቸክ አደረገ.... የማርቲኔሊን ጎል ሽረው ለማድሪድ ፍፁም ቅጣት ምት ሰጡ።

The Rest is History 😂!

Address

Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ąďåñė Mėłęśę AM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ąďåñė Mėłęśę AM:

Share