14/11/2022
።ትናት
#ህዳር 3/2015 ዓ/ም
ደባርቅ ከተማ
የደባርቅ ከተማ ወጣት ስፖርት ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት የ2014 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃ ፀም ዙሪያ ሪፖርት የስፖርት ማህበራት ማደራጃ ማዘውተሪያ ስፍራዎች ስልጠናና ውድድር ቡድን መሪ አቶ እያያው ታደለ አቅርበዋል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ ለስፖርቱ ቅርብ ግንኙነት ካላቸውና የስፖርቱ ባለቤት ከሆኑ የትምህርት ቤት ስፖርት መምህራን፣ዳኞች፣የፕሮጀክት አሰልጣኞች፣የስፖርት ማህበር ኮሚቴዎች የተገኙ ሲሆን ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ሃሳብና አስተያየት አቅርበዋል።
በቅድሚያ በከተማችን ላይ በጦርነት ምክንያት ተቋረጦ የቆየው የስፖርት እንቅስቃሴ በ2015 ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን አመቻችቶና አፅድቶ ለተግባር ቢውል ወጣቱ ከአልባሌ ደባል ሱስ ከመጠመድ ይልቅ ከሱስ ነፃ ሆነው ወደ ስፖርቱ የመምጣት እድሉ የሰፋ ይሆናል ተብሏል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደገለፁት በከተማው ላይ የሚደረጉ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ለማጠንከር ሲባል ለዳኞች በቂ ስልጠና መሰጠት እንዳለበት ገልፀው በየትምህርት ቤቶችና ቀበሌዎች ተቀዛቅዞና ተቋርጦ ያለውን ስፖርት በማነቃቃት ብቁ ዜጋ መፍጠር እንደሚገባና በአሁን ወቅት ከገጠር ወደ ከተማ በአዲስ የተቀላቀሉትን ቀበሌዎች ጨምሮ ዘመናዊና ባህላዊ የስፖርት አይነቶች ዳብረውና ጎልተው መውጣትና ወጣቱን ለስፖርት ያለው ፍቅር እንዲጨምር ሰፊ ስራ መሰራት እንደሚጠይቅ ጠቅሰዋል።
በመጨረሻም ከስፖርት አማተሮች በተነሱ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ላይ ምላሽ በመስጠት የጋራ መግባባት የተደረሰ ሲሆን
የደባርቅ ከተማ ወጣት ስፖርት ባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ስጦታው ታጀበ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።