Coach Amare Muche

Coach Amare Muche Amhara Atheletics Infotement
Addis Ababa and Bahirdar
P.O.Box # #
Ethiopia
+251-913-75 78 57
http:tiktok.com/

09/09/2026

#ከህይወታችን ማራቅ ያለብን ተስፋና ብርታት የማይሰጡንን ሰወች (ሀሳቦች) ነው!!
#ወድቆ መነሳት አለ እመነኝ !!!
#ከወደቁበት ተነስቶ ማሸነፍ አለ!!!
#ከኋላ መሆን ማለት ነገ ወደፊት አንመጣም ማለት አደለም!!!
#ከፊት ስትሆን ከኋላ ያሉትን አክብር አለም ለሁሉም እኩል ናት የቀን ጉዳይ ጋብቻ ነው !!

።።።።።።። በርቱልኝ!!!።።።።።።

08/09/2026

#ምንም ያክል የተከበረ ሙያ ቢኖረው ፣
እንድ ሰው አንድአይነት ስራ ብቻ መስራት የለበትም !!!
@እኛ ሀገር

08/09/2026

✍️ ምርጦችን ብቻ በአንድ መድረክ የሚያፋልመው ውድድር!!

የዓለም አትሌቲክስ አዲስ ውድድር የሆነው የዓለም አትሌቲክስ አልቲሜት ሻምፒየንሺፕ World Athletics Ultimate Championship 2026 ውድድር የፊታችን አርብ በሃንጋሪ ዋና ከተማ ቡዳፔስትይጀምራል።

በአይነቱ ለየት ያለ እና ምርጦችን ብቻ በመድረኩ የሚያገናኝ አዲሱ ውድድር በፈረንጆቹ ከመስከርም 11 እስከ 13 የሚደረግ ሲሆን ሽልማቱም እጅግ ከፍ ያለ እና የአለም አትሌቲክስ በእስካሁን እድሜ ቆይታው ለአሸናፊዎች ሸልሞት የማያውቀው ውድድር ነው፡፡

ይህ ውድድር አትሌቶች በየውድድር አይነቱ ባላቸው ፈጣን ሰዓት እና ከዚህ ቀደም በፓሪስ ኦሊምፒክ እና በዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የሆኑት የሚፋለሙበት ነው።

ሀገርን ወክለው ጠቀም ያለ ሽልማት የሚያገኙበት ይህ ውድድር በአትሌቶች ኮታ ሳይሆን በሚወዳደሩበት ርቀት ባላቸው ጥሩ ሰዓት በርካታ አትኬቶች መሳተፍ የሚችሉበት ነው።

በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 150,000 ዶላር የሚያሸልም ታላቅ የዓለም አቀፍ ውድድር ይዘጋጃል።

የትራክ እና የሜዳ ላይ ተግባራትን አካቶ በ28 የውድድር አይነቶችን የተከሰተው ሻምፒየንሺፑ ቀዳሚ ሆኖ ላጠናቀቁ አትሌት 150ሺ ዶላር ይሸልማል።

ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ለሚያጠናቅቀው አትሌት 75ሺ ዶላር እና ሶተኛ ለሚወጣው አትሌት 40ሺ ዶላር ሽልማት ሸልማለው ሲል የዓለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል።

ለተከታታይ ሶስት ቀናቶች በሚደረገው ውድድሩ በመድረኩ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ተለይተው ታውቀዋል።

ፅጌ ዱጉማ እና ንግስት ጌታቸው በ800 ሴቶች ሀገራቸውን ወክለው ጠቀም ያለ ሽልማት ለመውሰድ ይፋለማሉ፡፡

በሴቶች 1ሺ 500 ሜትር በሚደረገው ፉክክር

በርቀቱ ተደጋጋሚ ጊዜ ያሸነፈቸውን ብርቄ ሀይሎምን ጨምሮ ሳሮን በርሄ፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ እና ወጠቷ ሀረገወይኒ ካላዩ ለማሸነፍ ይፋለማሉ፤

ሌላኛው በ5ሺ ሜትር ሴቶች የአለም አትሌቲክስ የመረጣቸው ኢትዮጵያኑ አትሌቶች መዲና ኢሳ፣ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ ልቅና አምባው፣አለሽኝ ባወቀ፣ሰናይት ጌታቸው እና ፋንታዬ በላይነህ

በተመሳሳይ ርቀት በወንዶች 5ሺ በሚደረገው ውድድር የአመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት የሆነው

አትሌት አዲሱ ይሁኔን ጨምሮ ወጣቱ ቢንያም መሀሪ እነደሚካፈል የዓለም አትሌቲክስ ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡

የሃንጋሪ ዋና ከተማዋ የሆነችው ቡዳፔስት ከ19ኛ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2023 በኋላ ይምታዘጋጀው ትልቅ የውድድር መድረክ ነው።

02/09/2026

#ጥያቄ???
ከጥያቄው በፊት የትምህርት ቤት ጓደኛዬን ኪዳነማርያም ብርሀኔ እና ምክትል ቢሮ ሀላፊው (ወንድሜን) አቶ ጋሻው ተቀባን በጥሩ ሁኔታ ስላቀረባቹህልን አመሰግናለሁ።

#ጥያቄ :- ሜዳው ተሻሽሎ በድጋሜ ሲሰራ (ሲታደስ) እሳቤው ሙሉ በሙሉ እግርኳስዊ ነው ይባላል? ለዛ ደግሞ አመላካች የሚመስለው በቀጥታ ከመልበሻ ክፍል ወደ ሜዳው ሲገባ ትራኩ ላይ የተነጠፈው ሰው ሰራሽ ሳር አንዱ ይመስለኛል?

:- መጀመሪያ ሲሰራ ከእግርኳስ ባሻገር ለአትሌቲክሱ ታስቦ የተሰሩ የመወርወሪያ ቦታወች (pad) እንዲቀሩ (አገልግሎት)እንዳይሰጡ ሆነዋል ይባላል ለምን?

:- ካፍ /ፊፋ ብቻ እንዲገመግሙ ከመስራት
የአፍሪካ /አለም አትሌቲክስ ሰወች አብረው እንዲገመግሙ ማድረግ አይቻልም ወይ?

ሜዳው ከእግርኳስ ባሻገር የአንድቀን አለማቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር እንዲዘጋጅበት ቢደረግ በአመት ውስጥ ከሚደረጉ የእግርኳስ ውድድር ገቢ ያልተናነሰ ገንዘብ እንደሚያስገኝ ማሰብ አይቻልም ወይ?
#ለምሳሌ አአ የተደረገው ግራንድ ፕሪክስ የአትሌቲክስ ውድድር ባንድ ቀን ገቢው ስንት እንደነበረ መጠየቅ ብትችሉ?

#በስተመጨረሻ ትዝብቴ የአትሌቲክስ experts እና አጋር አካላት ላይ ነው?

#ስፓርቱ የካድሬ ስራ ባይሆን ? . ❤🙏❤

Zewi may God bless you and help you grow into a wonderful person. You are truly amazing. ❤️🙏“Seeing you like this makes ...
31/08/2026

Zewi may God bless you and help you grow into a wonderful person. You are truly amazing. ❤️🙏

“Seeing you like this makes me happy.
❤️

30/08/2026

Address

Jijiga

Telephone

+251-913-75 78 57

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Coach Amare Muche posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Coach Amare Muche:

Shortcuts

Share

Category