GAMO MEDIA SPORT

GAMO MEDIA SPORT ከእውነተኛ ምንጭ የተረጋገጠ የስፖርት ዜና ምነገርበት ቻናል እንግድያውስ ምን ይጠብቃሉ ቤቱን ፎሎ በማድረግ ይቀላቀሉ

አስቶንቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆነአስቶንቪላ ፍሬይቡርግን 3ለ0 በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ።በቤሺክታሽ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ የእንግሊዙን ክለብ ድል ያበሰሩ...
20/05/2026

አስቶንቪላ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆነ

አስቶንቪላ ፍሬይቡርግን 3ለ0 በማሸነፍ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ።

በቤሺክታሽ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ የእንግሊዙን ክለብ ድል ያበሰሩ ግቦች ዩሪ ቲሊማንስ ፣ ኤሚ ቡንዲያ እና ሞርጋን ሮጀርስ አስገኝተዋል።

የአስቶንቪላን የበላይነት መግታት ያልቻለው የጀርመኑ ክለብ ፍሬይቡርግ የመጀመሪያ የአውሮፓ ውድድር የፍፃሜ ጨዋታው በሽንፈት ተደምድሟል።

አስቶንቪላ በአውሮፓ መድረክ ሲነግስ ከ44 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ቪሊ እኤአ ከ1982 ባየርን ሙኒክን አሸንፎ የዩሮፒያን ካፕ (አሁን ቻምፒየንስ ሊግ) ካሸነፈ በኋላ ዋንጫ የማንሳት እድል አልነበረውም።

"የዩሮፓ ሊግ ንጉስ" የሚል ቅፅል ስም ያገኙት የአስቶኝቪላው አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬይ አምስተኛ ዋንጫቸውን አንስተዋል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ከዚህ ቀደሞ ከሲቪያ ጋር ሦስት ፣ ከቪያሪያል ጋር ደግሞ አንድ ጊዜ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማሸነፋቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያ ቡና ወደ ድል ተመለሰኢትዮጵያ ቡና በ33ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብሩ ፋሲል ከነማን ገጥሞ 2ለ1 አሸንፏል።በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቡበከር...
20/05/2026

ኢትዮጵያ ቡና ወደ ድል ተመለሰ

ኢትዮጵያ ቡና በ33ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብሩ ፋሲል ከነማን ገጥሞ 2ለ1 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አቡበከር አዳሙ በፍፁም ቅጣት ምት ሀብታሙ አሸናፊ በጨዋታ የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል። ኪሩቤል ዳኜ የፋሲል ከነማን ብቸኛ ግብ አስመዝግቧል።

ከአራት ተከታታይ ድል አልባ ጨዋታዎች በኋላ ድል ያደረገው ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 46 አድርሷል። በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ጨዋታውን የተሸነፈው ፋሲል ከነማም በተመሳሳይ 46 ነጥብ ይዟል።

መቐለ 70 እንደርታ ወሳኝ ድል አሳካበ33ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐግብር ሸገር ከተማን የገጠመው መቐለ 70 እንደርታ 1ለ0 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው...
20/05/2026

መቐለ 70 እንደርታ ወሳኝ ድል አሳካ

በ33ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐግብር ሸገር ከተማን የገጠመው መቐለ 70 እንደርታ 1ለ0 አሸንፏል። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቦና አሊ የመቐለን ግብ 90+1 ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

ወራጅ ቀጠና የሚገኘው መቐለ 70 እንደርታ ድሉን ተከትሎ ነጥቡን ወደ 34 አሳድጓል። ሁለት ተከታታይ ጨዋታ የተሸነፈው ሸገር ከተማ 40 ነጥብ አለው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ተጋጣሚዎቹን ለይቷልየ2027 አፍሪካ ዋንጫ የምድብ የማጣሪያ ድልድል በግብፅ ካይሮ ይፋ ሆኗል።በቅድመ ማጣሪያው ሳኦቶሜን ያሸነፉት  ዋልያዎቹ ከሴኔጋል ፣ ሞዛ...
19/05/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ተጋጣሚዎቹን ለይቷል

የ2027 አፍሪካ ዋንጫ የምድብ የማጣሪያ ድልድል በግብፅ ካይሮ ይፋ ሆኗል።

በቅድመ ማጣሪያው ሳኦቶሜን ያሸነፉት ዋልያዎቹ ከሴኔጋል ፣ ሞዛምቢክ እና ሱዳን ጋር በምድብ 10 ተደልድለዋል።

በሦስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ የሚዘጋጀው የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎቹ መስከረም ወር ላይ ይጀምራሉ።

ፔፕ ጋርዲዮላን በኢንዞ ማሬስካ?ትናንት ምሽት የተሰማው ዜና ከማንችስተር ሲቲ አልፎ በመላው ዓለም ያሉ የእግርኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ የሳበ ነበር። በተአማኒነታቸው የተወደሱ በርካታ የእንግሊዝ...
19/05/2026

ፔፕ ጋርዲዮላን በኢንዞ ማሬስካ?

ትናንት ምሽት የተሰማው ዜና ከማንችስተር ሲቲ አልፎ በመላው ዓለም ያሉ የእግርኳስ አፍቃሪያንን ቀልብ የሳበ ነበር። በተአማኒነታቸው የተወደሱ በርካታ የእንግሊዝ ብዙሃን መገናኛ ፔፕ ጋርዲዮላ የውድድር ዓመቱ ሲጠናቀቅ የማንችስተር ሲቲ እህል ውሃው ያበቃል አሉ።

መቼ የሚለው ካለሆነ በስተቀር ፔፕ 10 ዓመታት የነገሰበትን ዙፋን ለሌላ ማስረከቡ የማይቀር ነው። የበርካቶችን ቀልብ የሳበው ፔፕ ምንም ፍንጭ አለመስጠቱ ይመስላል። የ55 ዓመቱ ስፔናዊው አሰልጣኝ ከጋዜጠኞች የሚቀርብለትን “ይህ የመጨረሻ የውድድር ዓመትህ ሊሆን ይችላል?’’ ጥያቄን የሚያልፈው ቀሪ የአንድ ዓመት ውል አለኝ በሚል ነበር።

ማንችስተር ሲቲ ይህ እንዲሆን ትልቁ ምኞቱ ነበር። ፔፕ እንዳለው ውሉን ቢጨርስ ይመርጣሉ ፤ ነገር ግን እርሱን መተካት የሚያስችል ስራ ቀድመው አከናውነዋል።

ታላቁ አሰልጣኛቸው እንዲቆይ ቢመኙም መጨረሻው መቃረቡን ቀድመው ተገንዝበዋል። ለዛም ነው የቀድሞ የሲቲ ወጣት ቡድን እንዲሁም የጋርዲዮላ ረዳት አሰልጣኝ የነበረው ኢንዞ ማሬስካን ለመሾም የተቃረቡት።

ፔፕ ጋርዲዮላ ከማንችስተር ሲቲ አልፎ በእንግሊዝ እግር ኳስ ውስጥ እንደ አብዮተኛ ይቆጠራል። በሁለት አስርተ ዓመታት የውሃ ሰማያዊዎቹ ቤት ቆይታው 20 ዋንጫዎቹን አሸንፏል። ከዋንጫዎቹ ብዛት በዘለለ ድሎቹ የመጡበት መንገድ በርካቶች የእርሱ ተከታይ እንዲሆኑ አድርጓል።

በእንግሊዝ ታችኛው ዲቪዚዮን የሚጫወቱ ክለቦች ሳይቀር አጨዋወቱን ኮርጀዋል። አንዳንዶች በእንግሊዝ በፈጠረው ተጽዕኖ ምክንያት ከሰር አሌክስ ፈርጉሰንም በላይ የምንጊዜውም ምርጥ አሰልጣኝ መባል አለበት የሚሉ በርካታ ናቸው።

100 ነጥብ አምጥቶ ዋንጫ ያነሳ ፤ በእንግሊዝ ሆኖ የማያውቅ አራት ተከታታይ የሊግ ዋንጫ ያሸነፈ ሌሎች በርካታ ተዓምሮችን ያሳየ አሰልጣኝ የምንጊዜም ምርጥ መባል እንዳለበት ይከራከራሉ።

ይህን ምጡቅ አሰላጣኝ መተካት ለማንችስተር ሲቲ ፈታኝ ቢሆንም ለጊዜው በእርሱ ስር የተማረውን ኢንዞ ማሬስካን መርጠዋል። ጣልያናዊው አሰልጣኝ የሲቲን ቤት በደንብ ጠንቅቆ ቢያውቅም ፔፕን መተካት ፈታኝ ይሆንበታል። ሌስተር ሲቲን ወደ ፕሪምየር ሊግ ማሳደግ እና በቼልሲ ያገኛቸው የኮንፍረንስ እና የዓለም ክለቦች ዋንጫ በቂ ላይሆን ይችላል። ይህ ሁሉ ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ነው።

ለጊዜው የፔፕ ጋርዲዮላም ሆነ የማንችስተር ሲቲ ሙሉ ትኩረት ቀሪ ሁለት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

ኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ‎በ33ኛው ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡በአዲስ አበባ ስታዲየ...
19/05/2026

ኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ አቻ ተለያዩ

‎በ33ኛው ሳምንት ሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን እና ወላይታ ድቻ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 7 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ነው ጨዋታቸውን ያጠናቀቁት፡፡

ሰበር ዜና | ኢንዞ ማሬስካ የማንስተር ሲቲ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ!ጣልያናዊው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ፔፕ ጋርዲዮላን በመተካት አዲሱ የማንቸስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ከስምምነት ላይ...
19/05/2026

ሰበር ዜና | ኢንዞ ማሬስካ የማንስተር ሲቲ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ!

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ፔፕ ጋርዲዮላን በመተካት አዲሱ የማንቸስተር ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ተረጋግጧል።

ማሬስካ በኢቲሃድ ስታዲየም የ3 ዓመታት ኮንትራት እንደሚፈራረሙ ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ ዘግቧል።

ማሬስካ ቀደም ሲል በማንቸስተር ሲቲ በፔፕ ጋርዲዮላ ስር በረዳት አሰልጣኝነት በስኬት መስራታቸው ይታወሳል። የቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኝ አሁን ወደ ቀድሞ ቤታቸው በዋና አሰልጣኝነት ለመመለስ ተቃርበዋል።

ቦርንማውዝ ከማንቼስተር ሲቲ‎በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ምሽት 3 ሰዓት ከ30 ላይ ቦርንማውዝን ይገጥማል፡፡በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮ...
19/05/2026

ቦርንማውዝ ከማንቼስተር ሲቲ

‎በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ምሽት 3 ሰዓት ከ30 ላይ ቦርንማውዝን ይገጥማል፡፡

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንቼስተር ሲቲ በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየት የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በምሽቱ ጨዋታ ነጥብ የሚጥል ከሆነ አርሰናል የ38ኛ ሳምንት ጨዋታውን ሳያደርግ የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

ቦርንማውዝ በበኩሉ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት የሚያደርገው ፉክክር በጨዋታው ይጠበቃል፡፡

ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን አሸነፈ።በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ፋሲል ከነማን ከአዳማ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ በፋሲል ከነማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 3ለ1 ነው ያሸነ...
16/05/2026

ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን አሸነፈ።

በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ፋሲል ከነማን ከአዳማ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ በፋሲል ከነማ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

ፋሲል ከነማ አዳማ ከተማን 3ለ1 ነው ያሸነፈው።

የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ግቦች በ35ኛው እና በ67ኛው ደቂቃ ታምራት ኢያሱ እና 90+9 ቃልኪዳን ዘላለም አስቆጥረዋል።

አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ደግሞ በ12ኛው ደቂቃ የፋሲል ከነማው አብዱልአዚዝ አማን በራሱ ግብ ላይ አስቆጥሯል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ::በ32ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2ለ1 አሸንፏል።በአዳማ ሳይንስ እና ቴ...
16/05/2026

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ኢትዮ ኤሌክትሪክን አሸነፈ::

በ32ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 2ለ1 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ኮንኮኒ ሀፊዝ እና እንዳልካቸው ጥበቡ የወልዋሎን ሁለት ግቦች አስቆጥረዋል። አቤል ሀብታሙ የኤሌክትሪክን ብቸኛ ግብ ያስገኘ ተጫዋች ነው።

ወልዋሎ ድሉን ተከትሎ ነጥቡን 39 አድርሷል። በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈት የገጠመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ደግሞ 45 ነጥብ ይዟል።

ማንችስተር ሲቲ የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ ሆነማንችስተር ሲቲ ቼልሲን በማሸነፍ ለስምንተኛ ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ ሆኗል።በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አንቷን ሴሜንዮ ያስቆጠረው ግብ ማ...
16/05/2026

ማንችስተር ሲቲ የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ ሆነ

ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን በማሸነፍ ለስምንተኛ ጊዜ የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ ሆኗል።

በዌምብሌይ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ አንቷን ሴሜንዮ ያስቆጠረው ግብ ማንችስተር ሲቲን ባለድል አድርጓል። ሲቲም በአጠቃላይ ያሸነፋቸውን የኤፍ ኤ ዋንጫዎች ስምንት አድርሷል።

የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን በውድድር ዓመቱ ያሸነፈው ሁለተኛ ዋንጫውም ሆኗል። ሲቲ በካራባኦ ካፕ አርሰናልን አሸንፎ ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።

ፔፕ ጋርዲዮላ በማንችስተር ሲቲ የ10 ዓመታት ቆይታው 20 ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል።

አሁንም በፕሪምየር ሊጉ የዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ሲቲ የፊታችን ረቡዕ ከቦርንማውዝ ጋር ይጫወታል።

በጊዜያዊ አሰልጣኝ ካሉም ማክፋርሌን የተመራው ቼልሲ በርካቶች ከጠበቁትም በላይ ቢፎካከርም ማሸነፍ አልቻለም። የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በመጨረሻ ካደረጋቸው አራት የኤፍ ኤ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታዎች አንዱንም አላሸነፈም።

Address

Addis Abeba
Addis Abeba

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GAMO MEDIA SPORT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share