Haset Sport ሀሴት ስፖርት

Haset Sport ሀሴት ስፖርት ይህ ቻናል 24 ሰዐት ስፖርታዊ መረጃዎችን በፍጥነት ወደ እናንተ ያደርሳል።

የመጀመሪያ አጋማሽ : የጨዋታ እንቅስቃሴ - ስፔን በመጀመሪያው አጋማሽ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ ወስዳ የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቋል። - ስፔኖች በጨዋታ እንቅስቃሴ ፣ የኳስ ፍሰት እና ፍጥነት ከአር...
19/07/2026

የመጀመሪያ አጋማሽ : የጨዋታ እንቅስቃሴ

- ስፔን በመጀመሪያው አጋማሽ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ ወስዳ የመጀመሪያ አጋማሽ ተጠናቋል።

- ስፔኖች በጨዋታ እንቅስቃሴ ፣ የኳስ ፍሰት እና ፍጥነት ከአርጀንቲና ተሽለው ታይተዋል።

- አርጀንቲና በሁለተኛው አጋማሽ እንዳለፉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የሚያገኟቸውን የግብ እድል ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

- ስፔን የግራ መስመር ክፍል ተጫዋቿ ኩኩሬላ ወደ ፊት መስመር ተጠግቶ መጫወቱ አርጀንቲና በአምስት ተከላካይ እንድትጫወት አስገድዷታል።

- በዚህም የአርጀንቲና ተጫዋች በስፔን የመሐል ሜዳ ክፍሉ ላይ ጫና እንዳያደርግ አድርጎታል።

- ስፔን በመጀመሪያው አጋማሽ በነበራቸው እንቅስቃሴ ከኳስ ጋር እና ከኳስ ውጪ ተጋጣሚያቸውን ተጭነው ሲጫወቱ ተመልክተናል።

https://www.youtube.com/watch?v=uc5HuWUHUDs
23/06/2026

https://www.youtube.com/watch?v=uc5HuWUHUDs

𝘼𝙂𝙍𝙀𝙀𝘿 |የማቲያስ ፈርናንዴዝ የዝውውር ጦርነት|ተጫዋቹ ONLY UNITED ብሏል|የዝውውር ዜናዎች|TRA...

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው  ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ...
15/06/2026

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው የተለያዩ ባህላዊ እና ሌሎች ይዘቶቸ ያሏቸው የሙዚቃ ሥራዎችን ለአድማጭ ተመልካች ያበረከተ ሲሆን ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ነበር።

ከሞት አፋፍ እስከ ሀገርን ወክሎ ጎል ማስቆጠር... ከዛሬ ስድስት አመታት በፊት ራውል ሂሚኔዝ በህይወት እና በሞት መካከል ነበር። ዛሬ ላይ ግን በአለም ዋንጫው ሀገሩን ሜክሲኮ ወክሎ ጎል አ...
12/06/2026

ከሞት አፋፍ እስከ ሀገርን ወክሎ ጎል ማስቆጠር...
ከዛሬ ስድስት አመታት በፊት ራውል ሂሚኔዝ በህይወት እና በሞት መካከል ነበር። ዛሬ ላይ ግን በአለም ዋንጫው ሀገሩን ሜክሲኮ ወክሎ ጎል አስቆጥሯል።
ሂሚኔዝ ከ6 አመታት በፊት ክለቡ ወልቭስ ከ አርሰናል ጋር ሲጫወት አሰቃቂ የጭንቅላት ጉዳት አጋጥሞት ከሜዳ ወጣ። በሀኪሞች በመትረፉ እድለኛ እንደሆመ ተነገረው። ለ9 ወራት ያህልም ከሜዳ ርቆ ህክምና ሲከታተል ቆየ። ተመልሶ ወደሜዳ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮም ታዲያ ጭንቅላቱ ላይ መከላከያ ' head guard' ማሰር ነበረበት። አሁን ድረስም' head guard' አስሮ ይጫወታል።
ትላንት ምሽት በ2026ቱ አለም ዋንጫ ሀገሩ ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን ባሸነፈችበት ጨዋታም ሁለተኛዋን ጎል አስቆጠረ፤ ለራሱ ደግሞ በአለም ዋንጫ ያስቆጠረው የመጀመሪያው ጎል ሆኖ ተመዘገበለት። ከጎሏ በኋላም ደስታው እምባውን መቆጣጠር እስኪያቅተው ድረስ እንደነበር በቴሌቭዥን ስክሪኖቻችንን ተመለከትን።

አርሰናል ከፒኤስጂ እያደረጉ የሚገኙትን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ 1ለ0 እየመሩ ወደ እረፍት አምርተዋል። ካይ ሀቨርትዝ አርሰናልን ቀዳሚ ያደረገች ግብ በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃ አስቆጥሯል። ⚽️...
30/05/2026

አርሰናል ከፒኤስጂ እያደረጉ የሚገኙትን የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ 1ለ0 እየመሩ ወደ እረፍት አምርተዋል።

ካይ ሀቨርትዝ አርሰናልን ቀዳሚ ያደረገች ግብ በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃ አስቆጥሯል።

⚽️ የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ፒኤስጂ 77% - 23% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

- ፒኤስጂ በመጀመሪያው አጋማሽ ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ማድረግ የቻለው 1️⃣ ጊዜ ነው።

- አርሰናል በመጀመሪያው አጋማሽ በፒኤስጂ የፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውስጥ መግባት የቻለው 4️⃣ ጊዜ ነው።

ይገምቱ ይሸለሙ20,000 birrለመሸለም 1 FOLLOW ያድረጉ2 SHARE ያድርጉመልካም ዕድል  #ይገምቱይሸለሙ
18/05/2026

ይገምቱ ይሸለሙ
20,000 birr
ለመሸለም
1 FOLLOW ያድረጉ
2 SHARE ያድርጉ
መልካም ዕድል
#ይገምቱይሸለሙ

👏🇵🇹💥ብሩኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖ 20ኛው አሲስት ደፈነውውውውውው ሪከርዱን መጋራት ቻለ ምቤሞ በመጨረሻም ካሰውው አሁን ፖርቹጋላዊዉ ነበልባል የምንጊዜም ብቸኛው ባለሪከርድ ለመሆን ...
17/05/2026

👏🇵🇹💥ብሩኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖኖ 20ኛው አሲስት ደፈነውውውውውው ሪከርዱን መጋራት ቻለ ምቤሞ በመጨረሻም ካሰውው አሁን ፖርቹጋላዊዉ ነበልባል የምንጊዜም ብቸኛው ባለሪከርድ ለመሆን እነሆ 1 አሲስት ብቻ በቂው ነው።

ይህንን ፎቶ ዕውነተኛ የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ዝም ብለው አያልፉትም።
17/05/2026

ይህንን ፎቶ ዕውነተኛ የማን.ዩናይትድ ደጋፊዎች ዝም ብለው አያልፉትም።

ማንችስተር ሲቲ ሻምፒዮን ሆኗል ! በእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል። የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ጎል አንቶይን ሴሜኒዮ አስቆጥ...
16/05/2026

ማንችስተር ሲቲ ሻምፒዮን ሆኗል !

በእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ማንችስተር ሲቲ ቼልሲን 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ጎል አንቶይን ሴሜኒዮ አስቆጥሯል።

የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን በውድድር ዘመኑ ሁለተኛ የሀገር ውስጥ ዋንጫውን አሳክቷል።

ማንችስተር ሲቲ 8️ኛ የኤፌ ካፕ ዋንጫውን ሲያሸንፍ ቼልሲ በበኩሉ በተከታታይ ለአራተኛ ጊዜ የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ተሸንፏል።

የ200 ሚሊዮን ፓውንድ ፍልሚያ በዌምብሌይ ሊካሄድ ቀን ቆርጧል!   ሀል ሲቲ vs ከሳውዝሃምፕተን በእግር ኳስ ዓለም በገንዘብ መጠኑ እጅግ ግዙፉና "ውዱ" ጨዋታ ተረጋግጧል! የሻምፒዮንሺፕ የ...
14/05/2026

የ200 ሚሊዮን ፓውንድ ፍልሚያ በዌምብሌይ ሊካሄድ ቀን ቆርጧል!
ሀል ሲቲ vs ከሳውዝሃምፕተን
በእግር ኳስ ዓለም በገንዘብ መጠኑ እጅግ ግዙፉና "ውዱ" ጨዋታ ተረጋግጧል! የሻምፒዮንሺፕ የፕሌይ-ኦፍ ፍጻሜ በዌምብሌይ ስታዲየም ሀምሌ 15 በዕለተ ቅዳሜ ሀል ሲቲን ከሳውዝሃምፕተን ጋር ያገናኛል።

አሸናፊው ቡድን ወደ ፕሪሚየር ሊግ ከማደጉ ጋር ተያይዞ ቢያንስ 200 ሚሊዮን ፓውንድ ገቢ ያስገባል! ይህም ጨዋታውን በዓለም ላይ በገንዘብ ረገድ እጅግ ማራኪው ጨዋታ ያደርገዋል።
ሀል ሲቲ ሚልዎልን አሸንፎ ሲያልፍ፣ ሳውዝሃምፕተን ደግሞ በጭቅጭቅ የታጀበውንና ሚድልስቦሮን የገጠመበትን ጨዋታ ድል አድርጎ ለፍጻሜው ደርሷል። በፍፃሜው ሳዉዝሃምተን ከሃል ሲቲ ጋር ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለማደግ ግንቦት 15 በዌምብሌይ ይፋለማሉ።

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Haset Sport ሀሴት ስፖርት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category