FMC Sport

FMC Sport Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FMC Sport, Sports, Addis Ababa.

ሊቨርፑል ከኢፕስዊች ታውንአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይጀምራል፡፡በዚህም ሊቨርፑ...
04/09/2026

ሊቨርፑል ከኢፕስዊች ታውን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሦስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይጀምራል፡፡

በዚህም ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ከኢፕስዊች ታውን ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

በአንዶኒ ኢራኦላ የሚመራው ሊቨርፑል የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ድል ለማሳካት ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

ሊቨርፑል በሊጉ ያደረጋቸውን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ሁለት አቻ በሆነ ተመሳሳይ ውጤት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ተጋጣሚው ኢፕስዊች ታውን በበኩሉ ወደ ድል ለመመለስ የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

በመጀመሪያ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ድል የቀናው ኢፕስዊች ታውን በሁለተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር በማንቼስተር ዩናይትድ 5 ለ 2 በሆነ ሰፊ ውጤት መሸነፉ አይዘነጋም፡፡

ሪቻርልሰን ከቶተንሃም ስብስብ ውጪ ሆነአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሪቻርልሰን ከቶተንሃም ሆትስፐር ስብስብ ውጪ ሆኗል።አሰልጣኝ ሮቤርቶ ...
03/09/2026

ሪቻርልሰን ከቶተንሃም ስብስብ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሪቻርልሰን ከቶተንሃም ሆትስፐር ስብስብ ውጪ ሆኗል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በቅርቡ ሪቻርልሰን ክለቡን ለመልቀቅ ጥያቄ ማቅረቡን መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

የ29 ዓመቱ ተጫዋች በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ስሙ ከኤቨርተንን ጋር ሲያያዝ ቆይቷል።

ሪቻርልሰን ለቶተንሃም ሆትስፐር 103 ጨዋታዎችን አድርጎ 27 ግቦችን አስቆጥሯል።

የተጫዋቹ ቀጣይ ማረፊያ የት ይሆናል የሚለው ይጠበቃል።

ጋብሬል ማርቲኔሊ አል ሂላልን ተቀላቀለ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ማርቲኔሊን ከአርሰናል ...
03/09/2026

ጋብሬል ማርቲኔሊ አል ሂላልን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል ብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ጋብሬል ማርቲኔሊን ከአርሰናል ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

አል ሂላል ለጋብሬል ማርቲኔሊ ዝውውር 60 ሚሊየን ፓውንድ ለአርሰናል መክፈሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጋብሬል ማርቲኔሊ በ2025/26 የውድድር ዓመት ከአርሰናል ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱ ይታወሳል።

የማርቲኔሊ የዝውውር ሂሳብ የአርሰናል የተጫዋች ሽያጭ ክብረ ወሰን በመሆን ተመዝግቧል።

አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን በፈረንጆቹ 2017 ሊቨርፑልን በ35 ሚሊየን ፓውንድ በመቀላቀል የክለቡ የተጫዋች ሽያጭ ክብረ ወሰን ይዞ መቆየቱ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች ብቻ የካራቴ ውድድር ተካሄደ  አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጄ.ኪ.ኤስ ኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያ...
03/09/2026

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች ብቻ የካራቴ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጄ.ኪ.ኤስ ኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ካራቴ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የመጀመሪያው የሴቶች ብቻ የካራቴ ውድድር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በዚሁ ወቅት የጄ.ኪ. ኤስ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሰለሞን ዘውዱ እንዳሉት፤ ውድድሩ ፌዴሬሽኑ ከያዘው ሴት ስፖርተኞችን የማብቃት እቅድ አካል አንዱ ነው።

በውድድሩ ካዛና ክለብ በካታ ምድብ አንድ ወርቅ፣ አንድ ብር እና አንድ የነሀስ ሜዳልያዎችን በማግኘት የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል፡፡

በውድድሩ ካንኩ ዳይ ክለብ በአንድ ወርቅ እና አንድ ብር 2ኛ እንዲሁም ዊነር ክለብ በአንድ ወርቅ እና ሁለት ነሀስ ሜዳልያዎች 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የፋይት ውድድር 3 የወርቅ ሜዳልያዎችን የወሰደው ዊነር ክለብ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

በውድድሩ ከ8 ቡድኖች የተውጣጡ 56 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል።

በዳዊት መሐሪ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነሐሴ ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ይፋ ሆኑአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት የነሐሴ ወር ም...
03/09/2026

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነሐሴ ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት የነሐሴ ወር ምርጥ አሰልጣኝ እጩዎች ይፋ ሆነዋል።

በዚህም መሰረት፡- አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ፣ ዣቢ አሎንሶ፣ ኢንዞ ማሬስካ እና ሰርጌጅ ጃኪሮቪች በእጩነት ቀርበዋል፡፡

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነሐሴ ወር ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት የነሐሴ ወር ምር...
03/09/2026

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነሐሴ ወር ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ2026/27 የውድድር ዓመት የነሐሴ ወር ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆነዋል።

በዚህም መሰረት፡- ሪያን ሼርኪ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ፣ ሪካርዶ ካላፊዮሪ፣ ኮል ፓልመር፣ ጇ ፔድሮ፣ ማማዱ ሳንጋሬ፣ ዞላኪስ እና ዊሳ በእጩነት የቀረቡ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ቶተንሃም ሆትስፐር ሙድሪክን ከቼልሲ አስፈረመ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቶተንሃም ሆትስፐር ዩክሬናዊውን ተጫዋች ሙድሪክን ከቼልሲ አስፈርሟል።የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተ...
01/09/2026

ቶተንሃም ሆትስፐር ሙድሪክን ከቼልሲ አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቶተንሃም ሆትስፐር ዩክሬናዊውን ተጫዋች ሙድሪክን ከቼልሲ አስፈርሟል።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር ተጫዋቹን ወደ ስብስቡ የቀላቀለው በውሰት ውል ነው።

የ25 ዓመቱ ተጫዋች በውሰት ውሉ መሰረት ለአንድ የውድድር ዓመት ያህል በሰሜን ለንደኑ ክለብ የሚቆይ ይሆናል።

ሙድሪክ በፈረንጆቹ 2023 ቼልሲን በ70 ሚሊየን ዩሮ መቀላቀሉ ይታወሳል።

ቶተንሃም ሆትሰፐር በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሳንድሮ ቶናሊ፣ ማቲያስ ፈርናንዴዝ፣ ሳቪኒሆ፣ ሮበርትሰን እና ኦማር ማርሙሽን የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ማስፈረሙ ይታወሳል።

በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ የሚመራው ቶተንሃም ሆትስፐር በሊጉ ያደረጋቸውን ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች መሸነፉ አይዘነጋም።

ማንቼስተር ሲቲ ንዳዬን ከኤቨርተን አስፈረመ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ ሴኔጋላዊውን ተጫዋች ኢሊማን ንዳዬ ከኤቨርተን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል። ንዳዬ ...
01/09/2026

ማንቼስተር ሲቲ ንዳዬን ከኤቨርተን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ ሴኔጋላዊውን ተጫዋች ኢሊማን ንዳዬ ከኤቨርተን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።

ንዳዬ በማንቼስተር ሲቲ ቤት ለአምስት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል።

ማንቼስተር ሲቲ ለ26 ዓመቱ ተጫዋች ዝውውር 65 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ አድርጓል።

ንዳዬ ለኤቨርተን ባደረጋቸው 67 ጨዋታዎች 15 ግቦችን አስቆጥሮ 4 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።

ማንቼስተር ሲቲ ኤንዞ ፈርናንዴዝን ከቼልሲ ለማሰፈረም ተስማማአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ አርጀንቲናዊውን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ኤንዞ ፈርናንዴዝ ከቼልሲ ለ...
01/09/2026

ማንቼስተር ሲቲ ኤንዞ ፈርናንዴዝን ከቼልሲ ለማሰፈረም ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ሲቲ አርጀንቲናዊውን የመሐል ሜዳ ተጫዋች ኤንዞ ፈርናንዴዝ ከቼልሲ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል።

ማንቼስተር ሲቲ ለ25 ዓመቱ ተጫዋች ዝውውር 125 ሚሊየን ፓውንድ እንደሚከፍል ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ኤንዞ በፈረንጆቹ 2023 በ105 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ከፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡

በአቤል ነዋይ

የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነውአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን የአሰልጣኞች ሙያ ማሻሻያ ስልጠና መ...
01/09/2026

የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን የአሰልጣኞች ሙያ ማሻሻያ ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ አማረ፣ የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ዳዊት አስፋውን ጨምሮ በርካታ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

‎እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቀጥለው ይህ ስልጠና በሀገር አቀፍ ደረጃ በምስረታ ላይ ለሚገኙ ክለቦች የአሰልጣኞች ግብዓትን ለማስፋት ያለመ መሆኑን ፌደሬሽኑ ገልጿል።

በተጨማሪም የአሰልጣኞቹን ሳይንሳዊና ሙያዊ እውቀት በማጠናከር ከክለብ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የወርልድ ቴኳንዶ ልማት መስፋፋት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

በሰለሞን በቀለ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FMC Sport posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category