03/09/2026
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከወደ አርጀንቲናዋ የበረራ አስተናጋጅ ጋር ያጋጠመውን አስቂኝ ገጠመኝ ተናገረ! 😂✈️
Folloe🙏🙏
አንድ የአርጀንቲና ስፖርት ጋዜጠኛ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ስለ አርጀንቲናውያን ደጋፊዎቹ እና ሁልጊዜ ስለሚነሳው የ"ሜሲ እና ሮናልዶ" ክርክር በጠየቀበት ወቅት፣ ክርስቲያኖ በቅርቡ በጉዞው ወቅት ያጋጠመውን አስቂኝ አጋጣሚ ፈገግ እያለ አጫውቷል።
🗣️ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እንደተናገረው፡
"በበርካታ አጋጣሚዎች በሆቴሎች ውስጥ በምንቆይበት ጊዜ ከሰራተኞች እና ከጽዳት አባላት ጋር በአን Elevator አብረን እንሳፈራለን፤ አብዛኞቹም ላቲኖዎች ናቸው። ለምሳሌ አሁን አንተ አርጀንቲናዊ ነህ፤ ትናንት በበረራችን ወቅትም አንዷ የአየር መንገድ ሰራተኛ (የበረራ አስተናጋጅ) አርጀንቲናዊት ነበረች።
እኔ ገና ሳያት አርጀንቲናዊት መሆኗን አውቄ ነበር! አርጀንቲናዊ መሆኗን ያወቅኩት ደግሞ እኔን ባየችበት መንገድ ነው!" 😂
ሮናልዶ አክሎም የበረራ አስተናጋጇን እንዴት እንዳነጋገራት ሲገልጽ፡
"አርጀንቲናዊ እንደሆንሽ እርግጠኛ ነኝ አልኳት፤ እሷም በግረመታ 'እንዴት አወቅክ?' ስትል ጠየቀችኝ። እኔም 'እኔን ያየሽበት መንገድ ይናገራል' አልኳት።
'እንዴት ነው ያየሁህ?' ስትለኝ፡ 'አየሽኝ እና በፍጥነት ፊትሽን ወደ ሌላ አዞርሽ፤ ይህም ማለት ክርስቲያኖን አትወጂውም ማለት ነው' አልኳት።" 😭😂
ክርስቲያኖ ጨምሮ ሲናገር፡ "በርካጥ የቀለድኩባት ሲሆን በመጨረሻም 'የእኔ የህይወት አጋር (ጆርጂና) አርጀንቲናዊት ናት፤ ስለዚህ ለእኔ ከአርጀንቲናውያን ጋር ልዩ ፍቅር እና ክብር አለኝ' ብዬ ነግሬታለሁ" ሲል ገልጻል።