09/06/2026
አርሰናል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዚህ ክረምት ቡድኑን የበለጠ ለማጠናከር ከውሳኔ መድረሱ ተነግሯል።
የክለቡ የበላይ ሀላፊዎች በሚኬል አርቴታ እና ቤርታ ጥያቄ ቡድኑ ለረጅም ጊዜ አሸናፊ እንዲሆን ለማገዝ መዘጋጀታቸው ተሰምቷል።
ይህንንም ተከትሎ የጁቬንቱሱን ተጨዋች ኬናን ይልድዝ ለማስፈረም ጠይቀው ነበር።
ይሁን እንጂጨጁቬንቱስ ተጨዋቹ እንደማይሸጥ ያሳወቀ ሲሆን መድፈኞቹ ፊታቸውን ወደ ሌላ ተጨዋች አዙረዋል ተብሏል።
መድፈኞቹ አሁን ላይ ወጣት ተስፈኛ ተጨዋች ለማስፈረም ፍለጋቸውን ማጠናከራቸው ተገልጿል።
ክለቡ ጥሩ ተጨዋች መሆን የሚችል እና ለዋናው ቡድን የሚጫወት አልፍ ሲልም ተሸጦ ትርፍ ማምጣት የሚችል ተጨዋች ማግኘት ይፈልጋል።
አርሰናል አሁን ላይ የሌስተር ሲቲውን ተጨዋች ጄርሚ ሞንጋ ለማስፈረም በጥረት ላይ ይገኛል።
በሌላ በኩል የፒኤስጂውን ተከላካይ ኢማኑኤል ምቤምባ ለማስፈረም እያጤኑ መሆኑ ተገልጿል።
የ 18ዓመቱ ተከላካይ ኢማኑኤል ምቤምባ በዚህ ክረምት ከኮንትራት ነፃ እንደሚሆን ተዘግቧል።
መረጃው የዘ አትሌቲክ ነው።
https://t.me/+w8RCswOtQzs4ZmY8
https://www.facebook.com/wawlovtad