09/01/2019
በዕለተ ረዕቡ በታላላቅ የአውሮፓ ጋዜጦች ላይ የወጡ በርካታ የዝውውር ዜናዎች፣ የተጠናቀቁ ዝውውሮች እንዲሁም ሌሎች እግርኴሳዊ ዜናዎች!
👉 ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜና እንዳያመልጣቹ ከታች Like ማረጉን አይርሱ!
═════════════════════════
⚽️የኤስሚላኑ አርጀንቲናዊ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጉዌዝን ወደ ቸልሲ ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሱዋል።የአሁኑ የሰማያዊዎቹ አለቃ ማውሪዚዮ ሳሪ እና የ 31 አመቱ አጥቂ ጎንዛሎ ሂጉዌን ከዚህ ቀደም በጣልያኑ ቡድን ናፖሊ አብረው መስራት ችለዋል።(Marca)
⚽️የቶተንሀሙ ሊቀመንበር ዳንኤል ሌቪ ዴኒማርካዊ አማካያቸው ላይ £225 million የዝውውር ዋጋ ለጥፈውበታል ተጫዋቹ በሬያል ማድሪድ መፈለጉን ተከትሎ።(AS - in Spanish)
፧
⚽️የቶተንሀሙ አጥቂ ፈርናንዶ ዮረንቴ በድጋሚ ወደ አትሌቲኮ ቢልባኦ የመመለስ እድል አጊንቱዋል።(Mirror)
፧
⚽️መሀመደድ ሳላህ የ 2018 የአፍሪካ ምርጡ ተጫዋች በመባል ተመርጡዋል።
፧
⚽️የአትሌቲኮ ቢልባኦው ዋና ሀላፊ Rafael Alkorta በ 2014 ከክለባቸው የለቀቀውን አማካያቸው አንድሬ ሄሬራን በድጋሚ ወደ አንደሉሲያ የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።(Cadena Ser, via Mail)
፧
⚽️ነገር ግን ሄሬራ ምናልባት በኦልትራፎርድ አዲሱ አሰልጣኝ ኦሊገነር ሶሻየር አሳምኖት በክለቡ ለሌላ ተጨማሪ አመታት ሊያቆየው ይችላል።(Sun)
፧
⚽️ማንችስተር ዩናይትድ የረጅም ግዜ ኢላማቸውን ሴኔጋላዊውን ተከላካይ ካሊዶ ኩሊባሊን ለማስፈረም እሰከ ሚመጣው ክረምት ለመጠበቅ ወስነዋል።(ESPN)
፧
⚽️ኢንተር ሚላን የማንችስተር ዩናይትድ ኢላማ የሆነውን የ 29 አመቱን የክንፍ መስመር ተጫዋቻቸውን ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል ከሱ የሚገኘውን ገንዘብ ወደ ክሮሺያዊው የሬያል ማድሪድ ኮከብ ሉካ ሞድሪች ለማዞር።(Tuttosport, via Calciomercato)
፧
⚽️የኢንተር ሚላኑ አርጀንቲናዊ አጥቂ ማውሮ ኢካርዲ የቸልሲው ባለቤት ሮማን አብረሃምኦቪች የጥሩ የዝውውር መስኮት ዋነኛው የዝውውር ፍላጎታቸው ነው።(Mirror)
፧
⚽️ባየርሙኒክ የ 18 አመቱን ሆላንዳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች Callum Hudson-Odoi ለማስፈረም ከዚህ ቀደም ካቀረቡት ገንዘብ በላይ £35 million አቅረበዋል።ታዳጊውም ከእስታምፎርድ ብሪጅ በዚህ በጥሩ የዝውውር መስኮት የመልቀቅ ፍላጎት አለው።(Guardian)
፧
⚽️ቸልሲ በውሰት በሲቪያ የሚጫወተውን ንብረትነቱ የኤስሚላን የሆነውን ፖርቹጋላዊ ውን አጥቂ አንድሬ ሲልቫን ማስፈረም ይፈልጋሉ ነገር ግን ስፔናዊውን አጥቂ አልቫሮ ሞራታን ለሲቪያ መስጠት ይጠበቅባቸዋል ለሲልቫ ተተኪ እንዲሆንላቸው ።(Sun)
፧
⚽️ኤቨርተን የፖርቶውን አልጄርያዊ አማካይ ያሲን ብራሂኒን እየተከታተሉት ነው በዚህ ሳምንት ሰኞ መልማዮቻቸውን ወደ ፖርቹጋል በመላክ ፖርቶ ኒያሶናልን 3-1 ሲያሸንፍ 2 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍም ተመልክተውታል። (Mirror)
፧
⚽️የበርንሌው ግብ ጠባቂ ጆ ኸርትን በውሰት ለመውሰድ ፕሪስቶን ኢላማቸው አድርገውታል።(Sun)
፧
⚽️ክሪስታል ፓላስ የቸልሲውን አጥቂ ታሚ አብረሃምን በውሰት መውሰድ ይፈልጋሉ የ 21 አመቱ አጥቂ በአሁን ሰዓት በአስቶንቪላ በውሰት ቢገኝም የፕርሜርሊጉን ክለብ ወልቭስን ይቀላቀላል ቢባልም ከዛ የመጣውን የውሰት ውል ጥያቄ ውድቅ አድርጉዋል። (Mirror)
፧
⚽️ሳውዝሀምፕተን የ 21 አመቱን የክንፍ መስመር ተጫዋች አድሞል ሉክማን ከኤቨርተን የማስፈረም ጠንካራ ፍላጎት አለው። (Star - via HITC)
፧
⚽️ፉልሀም የቸልሲውን እንግሊዛዊ ተከላካይጋሪ ካሂልን፣ናይጄሪያዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ቪክተር ሞሰስን እና እንግሊዛዊውን አማካይ ዳኒ ድሪንክ ወተርን የማስፈረም ፍላጎት አላቸው እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ሶስት ተጫዋቾች በአሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ምንም አይነት እድል እየተሰጣቸው አይደለም። (Love Sport Radio)
፧
⚽️የሊቨርፑሉ ተከላካይ ራፋኤል ካማቾ ከቀናት በፊት በ FA CUP ላይ ተሰልፎ የመጀመሪያ ጫወታውን ቢያደርግም ከመርሲሳይዱ ክለብ በመልቀቅ የፖርቹጋሉን ክለብ ስፖርቲንግ ሊዝበን በውሰት ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሱዋል።(Talksport)
፧
⚽️የዋትፎርዱ አማካይ አብዱላይ ዶኮሬ ወደ ፈረንሳዩ ክለብ ፓሪሴንጀርመን መዘዋወር ህልሙ እንደሆነ ተናግሯል።የ 26 አመቱ አማካይም ስሙ ከፒኤስጂ ጋር ተያይዞ መነሳት ከጀመረ ሰነባብቱዋል። (Mirror)
፧
⚽️የባርሴሎናው አማካይ ዴኒስ ሱዋሬዝ በዚህ በጥሩ የዝውውር መስኮት ወደ አርሰናል የመዘዋወር ጠንከር ያለ ፍላጎት አለው።(Mirror)
፧
⚽️ባርሴሎና ባለፈው ክረምት ያስፈርሙትን ብራዚላዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ማልኮምን ለመሸጥ ፍላጎት አላቸው።(Mundo Deportivo)
፧
⚽️ቶተንሀም የወልቭሱን የመስመር ተከላካይ ማት ዶሀርቲን እየተከታተሉት ነው ነገር ግን የ 26 አመቱ ተከላካይ በማልኮኔክስ በሚመጣው ቀናቶች ውስጥ ደሞዙ በእጥፍ ሊያድግለት ነው።(Irish Independent)
፧
⚽️ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በኦሊገነር ሶሻየር ተጋብዘው በመጡበት የፌስቲቭ ፔሬድ ጫወታ ግዜ ለተጫዋቾቹ ማንችስተር ዩናይትድን ወደ ቀድሞ ስኬታማነቱ እና የበላይነቱ መልሱት ብለው ነበር።(mirror)
፧
⚽️ማንችስተር ዩናይትድ ከባርሴሎና እና ከጁቬንቱስ ፉኩኩር ገጥሞታል የሮማውን ተከላካይ ኮስታስ ማኖላስን ለማስፈረም።ግሪካዊው ተከላካይም ከሮም የመልቀቅ ፍላጎት አለው።(express)
፧
⚽️ማንችስተር ዩናይትድ አማካያቸውን አንድሬ ፔሬራን በውሰት ለፊዮረንቲና ለማቅረብ እያጤኑ ነው የፊዮረንቲናውን ተከላካይ ኒኮላ ሚሊንኮቪችን ለማስፈረም።(mirror)
፧
⚽️ጆሴ ሞሪኒዮ ለሬያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፊዮረንቲኖ ፔሬዝ እኔን ወደ ማድሪድ በድጋሚ ለመመለስ ካሰብክ በቅድሚያ የመሀል ተከላካይ እና አጥቂ እንዲያስፈርሙ ነግሩዋቸዋል።(express)
፧
⚽️ቸልሲ የአጥቂ ክፍሉን ለማጠናከር ቁ.1 ኢላማቸው የበርንስማውዙ አጥቂ ካሉም ዊልሰን ነው አልቫሮ ሞራታ በዚህ ወር የሚለቅ ከሆነ።ነገር ግን የኤዲሆው ቡድን ለተጫዋቹ ዝውውር ከ £50million እስከ £70million ይፈልጋሉ ለእንግሊዛዊው ኢንተርናሽናል።(star)
፧
⚽️አርሰናል የቸልሲ ኢላማ የሆነውን የካግላሪውን አማካይ ኒኮላስ ባሬላን ለማስፈረም መጠየቃቸውን ኮሬራ ዴሎ ስፖርት ዘግቡዋል።(mail)
፧
⚽️ባርሴሎና £67 million በማውጣት በዚህ ሳምንት የአያክሱን ባለተሰጦ አማካይ ፍራንክ ዲጆንግን ዝውውር ይጨርሳል።(mail)
፧
⚽️ሊዮናል ሜሲ እና ሴስክ ፋብሪጋስ ጄራርድ ፒኬ በገዛው አንዶራ በተባለው ቡድን ውስጥ ድርሻ አላቸው::ክለቡም በአሁኑ ሰዓት በካታሎን ፕርሜር በአምስተኛው እርከን ላይ እየተሳተፉ ይገኛል::
፧
⚽️የቸልሲ ክለብ ባለቤት ሮማን አብረሃምኦቪች በዚህ በጥር እና በቀጣዩ ክረምት ከፍተኛ ገንዘብ በመመደብ አዝናኙን ናፖሊን በድጋሚ በእስታምፎርድ ብሪጅ ለመፍጠር ለሳሪ እገዛ ሊያደርጉላቸው ነው::[ሚረር]
፧
⚽️ባርሴሎና የ 19 አመቱን ተከላካይ ጄንክሌር ቶቢዶን ከቱሉስ ማስፈረማቸውን አረጋግጠዋል ነገር ግን የሚቀላቀላቸው በክረምት ነው::
፧
⚽️ሬያል ማድሪድ ከማንችስተር ሲቲ ባዘዋወረው አማካዩ ብራሂም ዲያዝ ላይ £674 million የውል ማፍረሻ ሊለጥፉበት ነው::