13/05/2023
" ሀላንድን እንዲያስፈርሙ ደውዬ ነበር "
የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ አሊ ጎነር ሶልሻየር ሞልድ እያሉ ያሰለጥኑት የነበረውን ኤርሊንግ ሀላንድ ማንችስተር ዩናይትድ እንዲያስፈርሙ ደውለውላቸው እንደነበር ተናግረዋል።
አሊ ጎነር ሶልሻየር በንግግራቸውም " ማንችስተር ዩናይትድን ለማሰልጠን ከመረከቤ ስድስት ወራት በፊት ለማንችስተር ዩናይትድ ደውዬላቸው ነበር ፣ እናም ስለ አጥቂያችን ኤርሊንግ ሀላንድ ነግሬያቸው ነበር ነገር ግን እነሱ ሊሰሙኝ አልፈለጉም።
እኛ በወቅቱ ሀላንድን ለመሸጥ የጠየቅነው አራት ሚልዮን ፓውንድ ብቻ ነበር ነገር ግን እነሱ ሊያስፈርሙት አልፈለጉም።"ሲሉ ተደምጠዋል።
ለፈጣን ስፖርታዊ መረጃዎች በቴሌግራም ቻናላችን ይከታተሉን
✅ https://t.me/mnisport