Athletic coche federal police sports club

Athletic coche federal police sports club Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Athletic coche federal police sports club, Martial Arts School, Addise ABABA, Addis Ababa.

07/12/2025

በሥራ ቦታችሁ ላይ መፈጸም የሌለባችሁ 3 ስህተቶች!

1) በፍጹም የሥራ ባልደረቦቻችሁን ሁሉ ጓደኞቻችሁ አድርጋችሁ አታስቡ፣
2) በፍጹም ለሥራ ባልደረቦቻችሁ የግል ሚስጥሮቻችሁን አታካፍሉ፣
3) በምትሰሩበት መሥሪያ ቤት አሠራርና ፖሊሲ ባትስማሙ እንኳን በፍጹም ለሥራ ባልደረቦቻችሁ አትንገሯቸው።

የሥራ ቦታችሁ ማለት ለሰራችሁት ሥራ የሚከፍላችሁ ቦታ ነው። ስለሆነም ስራችሁን ሥሩ፣ ክፍያችሁን ውሰዱ፣ ወደ ቤታችሁ፣ አለቀ።

በሥራ ቦታችሁ የግድ የቅርብ ጓደኛ መመስረት አይጠበቅባችሁም። ሥራችሁን አክብሩ፣ በምትችሉት አቅም ምርጥ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን ኃላፊነት ተወጡ።

እንዲህ ማድረጋችሁ ለብዙ ነገር ይጠቅማችኋል።

1) ከተቀጠራችሁበት ቦታ ወጥታችሁ በራሳችሁ ለመስራት ትችሉ ዘንድ የራሳችሁን ውሳኔ ብቻ ተጠቅማችሁ በነጻነት እንድታደርጉት፣ እንዲሁም የሌሎችን ይሁንታ እንዳትጠይቁና በራሳችሁ የምትተማመኑ እንድትሆኑ ያደርጋችኋል።

2) በጓደኝነትና በቤተሰባዊ ቅርርቦች ምክንያት መሥሪያ ቤታችሁን እንደ "ምቾት ቀጠና" በመቁጠር ከለመዳችሁት ቦታ እንዳትወጡ የሚያደርጋችሁን ወጥመድ ትሰብራላችሁ፣

3) በሥራ ቦታችሁ ውስጥ በሚመጡ የኃላፊነት ውድድሮች፣ ስኮላርሺፖችና እድገቶች ለመሳተፍ ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ ለመሆን በችሎታችሁ እና በሥራችሁ ብቻ ለመወዳዳር ያስችላችኋል። ይህም ብዙ ሰው ጋር ዝምድና በፈጠራችሁ ቁጥር ቤተሰባዊነት ስለሚሰማችሁ በይሉኝታ እድሎችን አሳልፋችሁ ለሌሎች እንዳትሰጡ ያግዛችኋል።

4) በመሥሪያ ቤታችሁ ውስጥ በሚፈጠሩ ኪሳራዎች፣ ጥፋቶችና የሥራ ውድቀቶች አብራችሁ ተጠያቂ እንዳትሆኑ ያደርጋችኋል። ይህም ማለት በመሥሪያ ቤቱ ውስጥ በሚደርሱ ማንኛውም ጥፋቶች ቤተሰባዊ ቅርርብ በመኖሩ ብቻ ለሚደርሱ ጥፋቶች አብራችሁ ተሳታፊዎች ወይም ተወቃሾች ስለምትሆኑ፣ ሥራችሁ ላይ ብቻ ማተኮራችሁና ብዙ ቅርርብ አለመፍጠራችሁ አብሮ ከመፈረጅ ብሎም ከመቀጣት ያድናችኋል።

5) በሥራ ቦታችሁ ውስጥ "እምቢ/አይሆንም" የሚለውን አቋም ማንጸባረቅ እንድትችሉና በማትስማሙበት ነገር የራሳችሁን አቋም እንድታንጸባርቁ ያደርጋችኋል።

6) ሀሜተኝነት፣ ጭፍን ጥላቻን፣ ጭፍን ፍረጃንና አግላይነትን እንደ ቀላል ነገር እንዳትለማመዱ ያደርጋችኋል።

Dr. Hiwot ✅

06/12/2025
05/11/2025

Address

Addise ABABA
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Athletic coche federal police sports club posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share