Amir Kamil

Amir Kamil .

11/05/2026

ሚስኪኑን ህዝብ በመንፈሳዊ ፈውስ ስም ወደራስ የማስጠጋት ስልት!

​በብዙ የዓለማችን ክፍሎች (በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች) የሚኖረው ሙስሊም ከቁርዓንና ከሱና ይልቅ፣ ከአካባቢው ባህል ጋር በተቀላቀሉ አጉል እምነቶች የተተበተበ ነው። ሚሽነሪዎች ይህንን ሁኔታ "ፎልክ ኢስላም" (Folk Islam) በማለት ይጠሩታል። ይህ ማህበረሰብ ስለ ቲዎሎጂ አይጨነቅም፤ የሚያስጨንቀው በሽታ፣ ድህነት፣ መተት እና ክፉ መናፍስት ናቸው። ሚሽነሪዎች ይህንን ስነ-ልቦናዊ ፍርሃት በሚገባ በማጥናት፣ ሃይማኖታዊ ክርክርን ትተው ራሳቸውን እንደ "መንፈሳዊ ፈዋሽ" አድርገው ያቀርባሉ።

​ይህ ስልት በምሁራዊ አጠራሩ "Power Encounter" (የኃይል ግጭት) ይባላል። በህመም ለሚሰቃይ ወይም በመንፈስ ለታሰረ ሰው፣ መፍትሄው ክርስትና ውስጥ እንዳለ አድርጎ በተግባር ለማሳመን የሚደረግ የስነ-ልቦና ጫወታ ነው። ሰዎቹ ወደ ክርስትና የሚመጡት የሃይማኖቱን እውነትነት አምነው ሳይሆን፣ ጊዜያዊ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግራቸውን ለመፍታት በሚል ጉጉት ነው። ማህበረሰቡ በራሱ ዘልማዳዊ የእውቀት ክፍተት ውስጥ መዘፈቁን እንደ ትልቅ እድል በመጠቀም፣ የሰውን ስቃይና ፍርሃት የሃይማኖት መቀየሪያ ወጥመድ ማድረግ የሚሽነሪዎች የረጅም ጊዜ የተፈተነ ስልት መሆኑን ታሪክ በግልጽ ይመሰክራል።

​በቀጣዩ ክፍል የምንዳስሰው አጀንዳ፡

የቤተሰብን መሰረት በመናድ የሚደረግን ስልታዊ ስትራቴጂያቸውን በቀጣይ ክፍል - 8 በአላህ ፍቃድ እንመለከተዋለን።

​የመረጃ ምንጮች፦

• ​James S. D. Langford, "Some Principles of Christian Mission to Muslims", Chapter 5 (Folk Islam).

• ​Muslim Evangelism (Methods used in central Asia, 1997-1999).

​እውቀት ብርሃን ነው! ይህን ጠቃሚ ጸሁፍ ሌሎችም እንዲያነቡት ጹሁፉን ሼር (Share) ያድርጉ። አንድ ሼር የብዙዎችን ግንዛቤ ሊቀይር ይችላል!

11/05/2026
Arsenal 💪💪💪💪 🎉🎉🎉
05/05/2026

Arsenal 💪💪💪💪 🎉🎉🎉

Way always me But we don't give up 💪💪💪💪
20/04/2026

Way always me
But we don't give up 💪💪💪💪

Address

Addis Ababa
ADDIS

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amir Kamil posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category