23/06/2025
በ6ኛው መላ ኢትዮጵያ ጨዋታ አንዱ የስፖርት አይነት የነበረው የዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።
በውድድሩም በወንድም በሴትም የአዲስአበባ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ቡድን ሻምፒዩን (አሸናፊ) መሆን ችሏል። እንዲሁም አማራ ክልል በወንድ 2ኛ በሴት 3ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል። በተመሳሳይ ኦሮሚያ በሴት 2ኛ በወንድ 3ኛ ሆኖ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ ድሬዳዋ በወንድ በሴት እንዲሁም ትግራይ በወንዶች ተሳታፊ ሆነዋል።
በወንዶች የፍጻሜ ጨዋታውን የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ክቡር አቶ አንበሳው እንየው እና የዊልቼር ቅርጫት ኳስ የስራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተው ውድድሩን ተመልክተዋል በመልዕክታቸውም የስራ አስፈጻሚ አባላትን አመስግነዋል ስፖርተኞቹንም አበረታተዋል።
ሰኔ 16/2017 ዓ.ም
ጅማ