26/04/2026
ብልጽግና ፓርቲ ህዝቡ ሲያነሳቸው ለነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ የመጣ ፓርቲ ነው - ከንቲባ ተመስገን ደጄኔ
በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ይፋዊ የቅስቀሳ መድረክ ተካሂዷል።
ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒ እንዲሆን ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ተብሏል።
በመድረኩ የተገኙት የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጄኔ ብልጽግና ፓርቲ ህዝቡ ሲያነሳቸው ለነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ የመጣ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር ለነበሩ ችግሮች ምላሽ ከመስጠት ባሻገር ተሸክመን ለተሻገርናቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምላሽ እየሰጠ የሚገኝ ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል።
በቁጥር ብዛት ሳይሆን በሀሳብ ብዘሃነትና በላይነት የምያምነው ብልጽግና ፓርቲ ሀገር መምራት ከጀመረ ወዲህ ባሉት ጥቅት የለውጥ ዓመታት በርካታ ስኬቶች ተመስግቧል ብለዋል።
ከንቲባው ጨምረውም ፓርቲዉ በባለፉት ጥቅት ዓመታት ለህዝባችን ተስፋ ሰጪ የሆኑና ተጨባጭ ለዉጥ ያመጣ ፓርቲ እንደሆነም ገልጸው፣ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እና የኢትዮጵያን ዕድገት በላቀ ደረጀ ላይ ለማድረስ የብልጽግና ፓርቲ ሥራዎችን በጋራ ሊናበሥራዉ ይገባል ብለዋል።
የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊና ድጋፍ አመራር አቶ ንጋቱ ኬሃሞ በበኩላቸው መንግስት እንደ ሀገር የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በማለፍ ትላልቅ ሀገራዊ ልማቶችን እያከናወነ የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
የብልጽግና ፓርቲ ሰዉ ተኮር ፓርቲ በመሆኑ በሀገር ደረጀ በርካታ የልማት አጀንዳዎችን ነድፈዉ የሚንቀሳቀስና ለወደፊቱም በህዝብ ልማት ዉግንና ላይ ትኩረት ያደረገ ፓርቲ ስለሆነ የፓርቲዉ አባላት በመንግስት ጎን በመቆም የተያዘዉ ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲሣካ በቁርጠኝነት ሊንቀሳቃሱ ይገባል ብለዋል።
በመድረኩም ላለፉት ስድስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ያቀረቡት የከተማው የመንግስት ረ/ተጠሪና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታደለ ተፈራ የብልፅግና ፓርቲ በኢትዮጵያ ውስጥ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡና መልስ ሳያገኙ የቆዩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ በማድረግ ታሪክ የሰራ ፓርቲ መሆኑን ያነሱ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በዲፕሎማሲ ድሎችን በማስመዝገብ ላይ ነዉ ብለዋል።
አክለዉም የብልፅግና ፓርቲ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በድል በማጠናቀቅ ሁለንተናዊና ዘላቂ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ እንደሚያካሂድ ጠቁመው የከተማችን ህዝብ ብልፅግናን በመምረጥ የአካባቢያችንን ብልፅግና በቀጣይ አምስት አመታት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ መድረክ የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር እንደሆነና ዛሬ በሙሉ ህብረተሰባችን ዘንድ በሚታየው በጎ አስተሳሰብና ወትሮዉኑ በነበረን በሀሳብ አንድነት ሀገራዊ የሆኑ የልማት ተልዕኮዎችን ከዳር ለማድረስ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ግላዊ አመለካከቶችን በጋራ በማረም የብልጽግና ፓርቲ የልማት አጀንዳዎችን ማሣካት ያስፈልጋል ብለዋሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች።
በመጨረሻም በቀረበው ሰነድ መነሻ ከተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ማላሽና የቀጣይ አቅጣጫ በማሰቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገባው፦ የአመያ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።