04/07/2025
ሊቨርፑል አርማውን ዝቅ አድርጓል !
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የዲያጎ ጆታን ህልፈት ተከትሎ በክለቡ ውስጥ የሚገኘው አርማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጓል።
ደጋፊዎቹ በበኩላቸው ከአንፊል ስታዲየም አቅራቢያ አበባ በማስቀመጥ በተጫዋቹ ህልፈት ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።
የሊቨርፑል ተጨዋቾች እንዲሁ ሀዘናቸውን ሲገገልፁ ዳርዊን ኑኔዝ “ የተሰማኝን ህመም የምገልፅበት ቃል የለኝም “ ብሏል።
ዳርዊን ኑኔዝ አክሎም " ሁልጊዜም ከፈገግታህ ጋር አስታውስሀለሁ ምርጥ የቡድን አጋር ነበርክ።“ ብሏል።
የፖርቹጋሉ ክለብ ፖርቶ በተመሳሳይ በክለቡ አርማው ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ሀዘናቸውን እየገለፁ ነው።