Worku ዲቻ

Worku ዲቻ sport

The Bee's Worku ዲቻ
27/08/2026

The Bee's
Worku ዲቻ

ArsenalBG39‎🇧🇷 የአርሰናል አዲሱ ፈራሚ ብሩኖ ጉይማሬሽ በኤምሬትስ ከደጋፊዎች ጋር ትዉዉቅ አድርጓል።
10/08/2026

Arsenal
BG39
‎🇧🇷 የአርሰናል አዲሱ ፈራሚ ብሩኖ ጉይማሬሽ በኤምሬትስ ከደጋፊዎች ጋር ትዉዉቅ አድርጓል።

የጦና ንቦቹ ማሊያዊውን ሲኣካ ባጋዮኮን አስፈርመው የአማካዩን ኦግስቲን ኦክጄፋና የግብ ጠባቂውን ካዲም ኒዳዬን ውል አራዝመዋል!ለቀጣዩ የውድድር ዓመት እራሳቸውን በሚገባ በማጠናከር ላይ የሚገ...
02/08/2026

የጦና ንቦቹ ማሊያዊውን ሲኣካ ባጋዮኮን አስፈርመው የአማካዩን ኦግስቲን ኦክጄፋና የግብ ጠባቂውን ካዲም ኒዳዬን ውል አራዝመዋል!

ለቀጣዩ የውድድር ዓመት እራሳቸውን በሚገባ በማጠናከር ላይ የሚገኙት የጦና ንቦቹ የ28 ዓመቱን ማሊያዊውን የግራ መስመር ተመላላሽ ተጫዋች ሲኣካ ባጋዮኮን የግላቸውን ማድረግ ችለዋል።

ተጫዋቹ ፕሮፌሽናል የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው በፈረንጆቹ 2016 ዓ.ም በሀገሩ ክለብ በጆኢባ ኤ ሲ አድርጓል። ምርጥ ብቃቱን ያሳየው ተጫዋቹ በዛኑ አመት ሌላኛውን የሀገሩን ክለብ ስታድ ማሊየን ተቀላቅሎ መጫወት ችሏል።

የግሪኩ ክለብ አናጄኒሲ ካርዲሳ፣ የዩክሬኑ ክለብ ኤፍ ሲ ማይናይ፣ የሊቢያው ክለብ አል-ኢትሃድና የኢራቁ አል-ቃሲም ስፖርት ክለብ ተጫዋቹ በትልቅ ደረጃ ከተጫወተባቸው ክለቦች ውስጥ ይጠቀሳሉ።

ከ2025 ጀምሮ እስካሁኗ ጊዜ ድረስ ደግሞ በአልጄሪያው ክለብ ሙስታክባል ባላዲኣት ቆይታ አድርጓል።

ከ2015 ጀምሮ ደግሞ በማሊ ታዳጊ ብሔራዊ ቡድን እራሱን አሳይቶ ለዋናው ብሔራዊ ቡድን ከ2019 ጀምሮ ማገልገል ችሏል።

በተጨማሪም ክለባችን በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አስደናቂ ጊዜን ማሳለፍ የቻሉትን የአማካዩን ኦክጄፋ ኦግስቲንና የግብ ጠባቂውን ካዲም ንዳዬን ውል ማራዘም ችሏል።

Welcome Siaka Bagayoko! ⭐⭐⭐

የወላይታ ዲቻና የብሄራዊ ቡድኑ ግብ ጠባቂ ቢኒያም ገነቱ ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል። ባለፉት አመታት በወላይታ ዲቻ ምርጥ እንቅስቃሴ በማሳየት ግሩም ግብ ጠባቂ መሆኑን ያስመሰከረው ቢኒያም ገነቱ ...
30/07/2026

የወላይታ ዲቻና የብሄራዊ ቡድኑ ግብ ጠባቂ ቢኒያም ገነቱ ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል። ባለፉት አመታት በወላይታ ዲቻ ምርጥ እንቅስቃሴ በማሳየት ግሩም ግብ ጠባቂ መሆኑን ያስመሰከረው ቢኒያም ገነቱ ቀጣዩ መዳረሻው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኗል።

Good luck 🤞

የጦና ንቦቹ አንድ ተጫዋች አስፈርመው ከሌላኛው ተጫዋች ጋር በስምምነት ተለያይተዋል!ክለባችን በፍቅር ግዛቸውን ማስፈረሙን አረጋግጧል።በሲዳማ ቡና ታዳጊ ቡደን ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ወ...
29/07/2026

የጦና ንቦቹ አንድ ተጫዋች አስፈርመው ከሌላኛው ተጫዋች ጋር በስምምነት ተለያይተዋል!

ክለባችን በፍቅር ግዛቸውን ማስፈረሙን አረጋግጧል።

በሲዳማ ቡና ታዳጊ ቡደን ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ወደ አርባምንጭ ከተማ ከመጣ ወዲህ ጥሩ የሚባሉ የውድድር ጊዜዎችን ሲያሳልፍ የቆየው ፈጣኑ የመስመር አጥቂ በፍቅር ግዛቸው አሁን ከአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጋር አብሮ ለመስራት ማረፊያውን የጦና ንቦቹ ቤት አድርጓል።

ሌላኛ ተጫዋች ግብ ጠባቂው ቢኒያም ገነቱ ሲሆን ከክለባችን ጋር በጋራ ስምምነት ተለያይቷል።

ክለባችን ለተጫዋቹ ለነበረው ቆይታ ሲያመሰግን ለቀጣይ የእግርኳስ ጉዞው መልካሙን ተመኝቶለታል።

ያለፉትን ዓመታት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂ ወላይታ ዲቻ ተቀላቅሏል።
29/07/2026

ያለፉትን ዓመታት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ የነበረው የመስመር አጥቂ ወላይታ ዲቻ ተቀላቅሏል።

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 ይጀመራል!🤞
28/07/2026

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መስከረም 30/2019 ይጀመራል!🤞

አብነት ደምሴ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ተለያይተዋል ቀጣይ ማረፊያው የት ይሁን? ይጠበቃል
28/07/2026

አብነት ደምሴ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ተለያይተዋል ቀጣይ ማረፊያው የት ይሁን? ይጠበቃል

ክለባችን ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋች ውልም አራዝሟል!ሴኔጋላዊው የመሃል ተከላካይ አዳማ ዋዴ በቃል ደረጃ ክለባችንን ለመቀላቀል ተስማምቶ ቆይቶ የወረቀት ስራዎች ዛሬ ...
27/07/2026

ክለባችን ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአንድ ተጫዋች ውልም አራዝሟል!

ሴኔጋላዊው የመሃል ተከላካይ አዳማ ዋዴ በቃል ደረጃ ክለባችንን ለመቀላቀል ተስማምቶ ቆይቶ የወረቀት ስራዎች ዛሬ በመጠናቀቃቸው በይፋ የጦና ንቦችን ተቀላቅሏል።

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ቡደኑ ከተረከቡበት ጊዜ ወዲህ ጥሩ መሻሻል ያሳየውና እና ለቀጣይ የውድድር ዓመት ራሱን በማጠናከር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ክለባችን ወላይታ ድቻ ሴኔጋላዊ የመሃል ተከላካይ በሁለት ዓመት ውል ነው ያስፈረመው።

ተከላካዩ 1.94 ሜትር ቁመት ያለው ተጫዋቹ በትልቅ ሊግ ደረጃ በሀገሩ ክለብ ሳክሬ ጅማሮውን አድርጎ ለቱርኩ ኡምራኒየስፖር እና በጆርጂያው ሎኮሞቲቭ ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ሀገሩ ሴኔጋል ተመልሶ ለጉይዲያዋየ ፣ ለቀድሞ ክለቡ ሳክሬ እንዲሁም ለኤኤስሲ ጃራፍ ተጫውቷል።

በሁለተኛ ደረጃ ክለባችንን የተቀላቀለው ተጫዋች ደግሞ ሱሌይማን አህመድ ነው።

ተጫዋቹ መነሻውን አሶሳ ከተማ አድርጎ በሊጉ ደግሞ በአዳማ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ መቐለ 70 አንደርታና ቅዱስ ጊዮጊስ ተጫውቷል። በተጨማሪ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫና በቻን ተጫውቶ አሳልፏል።

ሌላኛው ኪዳኔ አሰፋ ሲሆን በክለባችን ለመቀጠል ውሉን አድሷል። ኪዳኔ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ከክለባችን ጋር ለመቀጠል ውሉን ፈርሟል።

ክለባችን ወላይታ ዲቻ ሴኔጋላዊው የመሃል ተከላካይ በይፋ አሰፈርሟል።
25/07/2026

ክለባችን ወላይታ ዲቻ ሴኔጋላዊው የመሃል ተከላካይ በይፋ አሰፈርሟል።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251942957879

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Worku ዲቻ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category