18/08/2026
በፊንፊኔ /አዲሳ'ባ በ1928 ዓ/ም በፋሽስት ጣሊያን ሰራዊት ብቻ ሳይሆን በመቶ ሽህ ባንዳ ጦር ጭምር የተወረረች ዘመን ነበር ፣ ለምሳሌ በዚህ ቪዲዬ የሚታየው 18 ሽህ የራስ ኃይሉ ባንዳ ጦር ሲሆን ይህን ወራሪ ባንዳ ወደ ፊንፊኔ ሲገባ በትራምፔት በማሲንቆ ጨዋታ በፊከራ ታጅቦ በፋሽስቱ ጀኔራል ጋሪቦልዲ የእንኳን ደህና መጣህ አቀባበል እንዲህ ተደርጎለት ነበር።
የኢትዮጵያ አርበኞች በተለይ ከ50 ሽ በላይ አርበኛ ሰራዊት ይመሩ የነበሩት ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ( አባቦራ) በፊንፊኔ የነበረው ከ100 ሽ በላይ በራስ ኃይሉ : በደጃዝማች ከበደ : በራስ ሙልጌታ : በደጃዝማች አያሌው ብሩ : በራስ ጌታቸው አባተ የሚመራው የባንዳ ጦር ከጣሊያን እኩል ጠራርገው እንደ ቃሪ አራግፈው ከፊንፊኔ ቢያባርሯቸው ኑሮ የባንዳ ሰፋሪ ጦር ፊንፊኔ ሰላሟን አይነሷትም ነበር ። በነገራች ላይ የሚያሳዝነው ታሪክ ሁሉም የእናት ጡት ነካሽ ባንዳዎች ጀግኖች ሃገር ወዳድ አርበኞች ነፃ በአወጡት ሃገር ከነፃነት ማግስት ከፍተኛ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።