ቤስት ስፖርት ኢትዮጵያ / Best Sport Ethiopia

ቤስት ስፖርት ኢትዮጵያ / Best Sport Ethiopia ቤስት ስፖርት በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ ስፖርታዊ ክንውኖች ዙርያ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ፤ የመጀመሪያዋ ባለቀለም የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ አጋር ሚዲያ

🔴የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚወቀስበትን የቪዛ ችግር በስኬት አጠናቋል🔴 ለስኬቱ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) አድናቆት እየቀረበላቸው ነው🔴ከሰባቱ ...
29/07/2026

🔴የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚወቀስበትን የቪዛ ችግር በስኬት አጠናቋል

🔴 ለስኬቱ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) አድናቆት እየቀረበላቸው ነው

🔴ከሰባቱ ኦፌሺያልስ የአምስቱም ቪዛ ማግኘታቸው ተረጋግጧል

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከቪዛ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ወቀሳ ሲቀርብበት ነበር፤እንደ ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያልም ተደጋጋሚ ዘገባ በመስራት ድርጊቱንና የፌዴሬሽኑን በተለይ ፅ/ቤቱ አሠራሩን እንዲያሻሽል የትችት ናዳ ስታወርድም ነበር፤

አሁን ደግሞ ፌዴሬሽኑ በተለይ የፅ/ቤቱ ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) የሚያስመሠግን ስራ በመስራታቸው በአደባባይ ልናመሠግናቸው ስኬታማ ስራቸውና የጋዜጠኝነት ሙያችን ግድ ይለናል።

ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከታማኝ ምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ መሠረት
እ.ኤ.አ ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3/2018 ዓ.ም በአሜሪካ ዩጂን ኦሪገን ለሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ለመሳተፍ የተመረጡና በዝግጅት ላይ የሚገኙ አትሌቶችና አሠልጣኞች ለጉዞ የሚያስፈልጋቸውን ቪዛ ሙሉ በሙሉ ከአሜሪካ ኤምባሲ ማግኘታቸውን አረጋግጠውልናል።

አትሌቶቹና አሠልጣኞቹ ቪዛ እንዲያገኙ በማድረጉ በኩል እንደ ፌዴሬሽን ጥረት ቢደረግም የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር)ለስኬቱ ሚናቸው ከፍተኛ እንደነበር እነዚሁ የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀውልናል።

እነዚሁ የመረጃ ምንጮቻችን ጨምረው እንደገለፁልን ፌዴሬሽኑ በተለይ ጉዳዩን በዋናነት የሚከታተሉት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) ባለፈው ከተፈጠረው ክፍተት ትምህርት በመውሰድና በቀጥታ ከሚመለከተው አካል ጋር ግንኙነት በመፍጠር የአትሌቶች፣የአሠልጣኞች፣የፌዴሬሽኑና የስፖርት ቤተሠቡ ስጋትና ራስ ምታት የሆነውን የቪዛ ችግር በማስወገድ ሙሉ የልዑካን ቡድኑ ነገ ከተቀጠሩት 7 ኦፊሺያልስ ውጪ ቪዛ አግኝተው ለጉዞ ዝግጁ መሆናቸውን በማረገጋገጥ በርካቶች ከወዲሁ የፅ/ቤት ኃላፊውን ለማመስገን ተገደዋል።

አትሌትቹና የአሠልጣኞች መቶ በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን አብረው ከሚጓዙት ሰባቱ ኦፊሺያሎች የአምስቱ የቪዛ ጉዳይም(Issued)መሆኑና የተጠናቀቀ ሲሆን ማብራሪያ የተጠየቀባቸው የቀሪዎቹ ሁለትና ሶስት የሚሆኑት ኦፊሺያሎችም በነገው ዕለት ተጠናቆ የልዑካን ቡድኑ እንደ ባለፈው በቪዛ ችግር ተንጠባጥቦ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ተሟልተው ወደ አሜሪካ ዩጂን ኦሪገን እንደሚጓዙ እነዚሁ ምጮቻችን አረጋግጠውልናል።

ከባለፈው ተሞክሮ የወሠደው ፌዴሬሽኑ በተለይ የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር)በውጭ ጉዳይ፣በውድድሩ አዘጋጆች(LOC) እና በወርልድ አትሌቲክስ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ አሠራርን ብቻ ከመከተል በመውጣት በዋናነት ከአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ጋር በቀጥታ ግንኙነት በመፍጠር በመጀመሪያ በቪዛ አጠያየቅና ፎርም አሞላል ዙሪያ የOnline ሰልጠና ከተወሠደ በኋላ ይሄንኑ ስልጠና ለአትሌቶቹና ለአሠልጣኞቹ በመስጠት በመቀጠልም ስለ እያንዳንዱ አትሌት 14 ገፅ አጭር ፕሮፋይል በፅ/ቤት ኃላፊው ተዘጋጅቶ በመላክና በቂ ግንዛቤ እኔዲኖር በማድረግ ከቪዛ ጋር በተያያዘ የነበረውን መጥፎ ታሪክ የቀየረ ስራ እኚሁ የፅ/ቤት ኃላፊ መስራታቸውና ለቪዛው መሳካት ትልቁን ሚና መጫወታቸውን የፌዴሬሽኑ ምንጮቻችን አሳውቀውናል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሚወቀስበትን የቪዛ ችግር መቶ በመቶ በስኬት በማጠናቀቁ ብዙዎችን ያስደሠተ ሲሆን ለስኬቱም የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት የፅ/ቤት ኃላፊው አመንሲሳ ከበደ(ዶ/ር) የቪዛ አጠያየቁን በመቀየርና በማዘመን ለስኬቱ አይነተኛ ሚና በመጫወታቸውና በቪዛ ጉዳይ ስሙ የጠለሸውንና ከህገ-ወጥ ዝውውር ጋር በተያያዘ አመኔታ አጥቶ የቆየውን የፌዴሬሽኑን ስምና ክብር የመለሠ ስራ በመስራታቸው ከየአቅጣጫው የአድናቆት ናዳ እየወረደባቸው ነው።

ለወቀሳ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ስራ ሲሰራም ለማመስገን የማትሠስተው ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል በዚህ ስኬታማ ስራ ላይ የተሳተፉትን አካላት በቀጣይ አነጋግረን ለመምጣት ጥረት የምናደርግ ይሆናል።

ፎቶ ክሬዲት:የኢ.አ.ፌ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ

27/07/2026

የዶናልድ ትራምፕን ስም በማንሳቴ የትችት ናዳ ወርዶብኛል። ... // ቻናል 1 ስፖርት //በቻናል 1 በ...

🔴ሁሉም ሊያነበው የሚገባ🔴አነጋጋሪ በሆነው የተጫዋቾች ዝውውር ዙሪያ የአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የግል ምልከታ✍️✍️በቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ስራ አስኪያጅና በአሁን ሠዓት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ም/ዋና ...
27/07/2026

🔴ሁሉም ሊያነበው የሚገባ

🔴አነጋጋሪ በሆነው የተጫዋቾች ዝውውር ዙሪያ የአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የግል ምልከታ

✍️✍️በቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ስራ አስኪያጅና በአሁን ሠዓት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ም/ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የግል ምልከታ

🔴በዚህ ሁለተኛ ክፍል በተጨዋቾች ዝውውር ጉዳይ መልካም ጅምሮችን በክፍል አንድ የገለፅናቸውን ችግሮችና የመችትሄ ሀሳቦች እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተጫዋቾች ዝውውር ሥርዓትን ከፊፋ (FIFA) የተጫዋቾች ደረጃና ዝውውር መመሪያ (RSTP) ጋር በማጣጣም ረገድ የሚበረታቱ በርካታ እርምጃዎችን ወስዷል።

🔴1. የፊፋ መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ በሀገር የተጫዋቾች ውል፣ ዝውውር እና የክለቦች መብትና ግዴታ በግልጽ እንዲመራ መመሪያዎችን አውጥቷል።

🔴2. የዝውውር መስኮትን በሥርዓት ማስተዳደር፤ የተጫዋቾች ምዝገባና ዝውውር በተወሰነ የጊዜ ገደብ ብቻ እንዲፈጸም በማድረግ የውድድር ፍትሃዊነትን ለማስጠበቅ ሞክሯል።

🔴3. የተጫዋቾች ውሎችን በፌዴሬሽኑ ማስመዝገብ፤ የተጫዋቾች መብት እንዲጠበቅና የውል ክርክሮች ሲኖሩ ሕጋዊ ማስረጃ እንዲኖር ስርዓት ዘርግቷል።

🔴4. የዲሲፕሊን እና የውሳኔ ሰጪ አካላትን ማጠናከር፤ በውልና በዝውውር ጉዳዮች የሚፈጠሩ ክርክሮችን በሕግ መሠረት ለመፍታት ተቋማዊ አደረጃጀቶችን ፈጥሯል።
በእግርኳስ ክለቦችና በተጨዋቾች የሚስተዋሉ የዝውውር ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው

🔴1. በውል ላይ ያለ ተጫዋችን በድብቅ ማነጋገር
አንድ ተጫዋች ከክለቡ ጋር ሁለት ዓመት ውል እያለው ሌላ ክለብ በስልክ ወይም በድብቅ በሆቴል በመገናኘት "ወደ እኛ ና፣ የበለጠ ገንዘብ እንሰጥሃለን" ብሎ ቢያነጋግረው፣ ይህ የፊፋን ሕግ የሚጥስ ተግባር ነው። ይህ ተጫዋቹ በክለቡ ላይ ትኩረቱን እንዲያጣ እና በቡድኑ ውስጥ ያለው መተማመን እንዲበላሽ ያደርጋል።

🔴መፍትሔ

ማንኛውም ክለብ ውል ላይ ያለ ተጫዋችን ከማነጋገሩ በፊት የተጫዋቹን ክለብ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት።
ፌዴሬሽኑ የፊፋ RSTP ደንቦችን በጥብቅ በማስፈጸም በድብቅ የሚደረጉ ድርድሮችን ሊያስቆም ይገባል።

ሕግ የጣሱ ክለቦችና ተጫዋቾች ላይ የገንዘብ ቅጣት፣ የዝውውር እገዳ ወይም ሌሎች የዲሲፕሊን እርምጃዎች መመሪያን መሰረት አድረጎ መወሰድ አለባቸው።

🔴2. ሕገ-ወጥ ደላሎች

ብዙ ጊዜ በፊፋ እውቅና የተሰጠው የተጫዋች ወኪል ሳይሆን ጓደኛ፣ ዘመድ ወይም "የጎዳና ደላላ" (በነገራችን ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት እዲያድግ ሌት ተቀን የሚለፉ ፕሮፌሽናል ስነ-ምግባራቸው ከፍ ያለ የተከበሩና ሙያቸውን ያሰከበሩ በርካታ የስፖርት ጋዜጠኞች በሀገራችን ያሉ ሲሆን ነገር ግን ጥቂቶች እራሳቸውን ጋዜጠኛ ብለው የመደቡ ስነምግባር የጎደላቸው የተጨዋች ድለላ ስራ ላይ የተሰማሩ እንዳሉም መረዳት ያስፈልጋል) ዝውውሩን ይመራሉ። ዋና ዓላማቸው የተጫዋቹ ጥቅም ሳይሆን የራሳቸውን ኮሚሽን ማግኘት ስለሆነ ተጫዋቹን በተደጋጋሚ ክለብ እንዲቀይር ያደርጉታል። ይህም የተጫዋቹን የሙያ እድገት ይጎዳል።

🔴መፍትሔ

በፊፋ ፈቃድ ያላቸው ወኪሎች (Licensed Football Agents) ብቻ በዝውውር ሂደት እንዲሳተፉ ማድረግ።
ፌዴሬሽኑ ፈቃድ ያላቸውን ወኪሎች ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ ማድረግ።
ሕገ-ወጥ ደላሎችን በሕግ መጠየቅና ከዝውውር ሂደት ማስወገድ።

🔴3. ሁለት ውል መፈረም
ለምሳሌ አንድ ክለብ ለተጫዋች በወር 200,000 ብር ለመክፈል ቢስማማ፣ ለፌዴሬሽኑና ለግብር ሰብሳቢው ቢሮ ግን 60,000 ብር የተጻፈበትን ሌላ ውል ቢያቀርብ፣ ይህ የግብር ማጭበርበር እና የሕግ ጥሰት ነው። ከጊዜ በኋላ ክርክር ቢፈጠር ፌዴሬሽኑ የሚያየው ሕጋዊ ሰነድ 60,000 ብር የተጻፈበትን ውል ስለሆነ ተጫዋቹ መብቱን ሊያጣ ይችላል።

🔴መፍትሔ

አንድ ሕጋዊ ውል ብቻ እንዲኖር እና በፌዴሬሽኑ እንዲመዘገብ ማድረግ።
ሁሉም ክፍያዎች በባንክ እንዲፈጸሙ ማድረግ።
የውል ማጭበርበር የሚፈጽሙ ክለቦችና ተጫዋቾች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ።

🔴4. የቅድመ-ውል ስምምነትን አለማክበር
አንድ ተጫዋች ከክለብ "ሀ" ጋር ሕጋዊ የቅድመ-ውል ስምምነት ፈርሞ ከቆየ በኋላ ሌላ ክለብ የበለጠ ገንዘብ ሲያቀርብለት ለመጀመሪያው ክለብ ሳያሳውቅ ከሁለተኛው ክለብ ጋር ቢፈርም ይህ የውል ጥሰት (Breach of Contract) ነው። በዚህ ሁኔታ ተጫዋቹም ሆነ ሁለተኛው ክለብ በፊፋ ሕግ መሠረት ሊጠየቁ ይችላሉ።

🔴መፍትሔ

ሁሉም የቅድመ-ውል ስምምነቶች በፌዴሬሽኑ በይፋ እንዲመዘገቡ ማድረግ።
ቅድመ-ውልን የሚጥሱ ተጫዋቾችና ክለቦች በፊፋ እና በፌዴሬሽኑ መመሪያ መሠረት ተገቢውን ቅጣት እንዲቀበሉ ማድረግ።

ክለቦች አዲስ ተጫዋች ከማስፈረማቸው በፊት የውል ሁኔታውን የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዲወጡ ማድረግ።
ክለቦች ዝውውርን በራሰቸው ቢሮ ዲጀታል በሆነ መንገድ የሚመሩበትን ሁኔታ በአስገዳጅነት እንፊፈፅሙት ማድረግ፡፡

🔴5. የደመወዝ መዘግየት

አንድ ክለብ ለ2 ወራት የተጫዋቹን ደመወዝ ካልከፈለ ተጫዋቹ በፊፋ መመሪያ (Article 14bis) መሠረት መብቱን መጠየቅ ይችላል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ተጫዋቾች ይህን መብት ሲጠይቁ ከቡድን ውጪ ይደረጋሉ ወይም ጫና ይደርስባቸዋል። በሌላ በኩል አንዳንድ ተጫዋቾችም የሕግ ሂደትን ሳይከተሉ ልምምድ በማቋረጥ የሙያ ሥነ-ምግባርን ይጥሳሉ።
መፍትሔ
ክለቦች የፋይናንስ አቅማቸውን አረጋግጠው ብቻ ተጫዋቾችን እንዲያስፈርሙ።

ደመወዝ በባንክ እና በተወሰነ ጊዜ እንዲከፈል ማድረግ።
ተጫዋቾች መብታቸውን በሕጋዊ መንገድ እንዲጠይቁ እንጂ ልምምድን በማቋረጥ ውላቸውን እንዳይጥሱ ግንዛቤ መፍጠር።
🔴6. የአጭር ጊዜ የተጫዋቾች ውል (2 ዓመት) ባህል እና የውል አስተዳደር ድክመት (Poor Contract Administration and Short-Term Contract Culture)
የፊፋ (FIFA) የተጫዋቾች ደረጃና ዝውውር መመሪያ (RSTP) አንቀጽ 18 መሠረት የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች የውል ጊዜ እስከ 5 ዓመት ነው፡፡ ይህ ድንጋጌ ክለቦች ተጫዋቾችን በረጅም ጊዜ ለማልማት፣ የቡድን መረጋጋት ለመፍጠር እና ከተጫዋቾች ዝውውር የኢኮኖሚ ጥቅም ለማግኘት እንዲችሉ ያግዛል።

🔴ያለው እውነታ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ግን አብዛኞቹ ክለቦች ከተጫዋቾች ጋር 2 ዓመት ውል ብቻ መፈረምን እንደ መደበኛ አሰራር ተቀብለዋል። ይህ በራሱ ሕገ-ወጥ አይደለም፤ ፊፋ የተጫዋቾች ደረጃና ዝውው መመሪያ (RSTP) አንቀጽ 18(2) መሠረት፣ የአንድ ፕሮፌሽናል ተጫዋች የውል ስምምነት ዘመን ቢያንስ እስከ ውድድር ዓመቱ (ሲዝኑ) ማብቂያ ድረስ መሆን ያለበት ሲሆን፣ ከፍተኛው የውል ዘመን ደግሞ ከአምስት ዓመት መብለጥ የለበትም ይላል።ሆኖም ይህ በተደጋጋሚ የሚታየው የ2 ዓመት ውል ባህል ከውድድር፣ ከክለብ አስተዳደር እና ከኢኮኖሚ አንፃር ትልቅ ድክመት ፈጥሯል።

🔴የሚፈጥረው ችግር

ክለቦች የረጅም ጊዜ የቡድን ግንባታ (Squad Building) ማከናወን ይቸገራሉ።
ተጫዋቾች በየሁለት ዓመቱ ክለብ መቀየርን ይለምዳሉ፤ ይህም የክለቦችን መረጋጋት ያናጋል።
ክለቦች ከተጫዋቾች ሽያጭ ሊያገኙት የሚገባቸውን የዝውውር ገቢ ያጣሉ።
በወጣት ተጫዋቾች ላይ ኢንቨስትመንት የማድረግ ፍላጎት ይቀንሳል።
የኢትዮጵያ ክለቦች በአፍሪካና በዓለም እግር ኳስ የተጫዋች ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም መፍጠር አይችሉም።

🔴መፍትሔ

ክለቦች የተጫዋቹን ዕድሜ፣ ብቃት፣ የዕድገት እቅድና የክለቡን ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ ከ3 እስከ 5 ዓመት የሚደርስ የውል ፖሊሲ እንዲተገብሩ ማበረታታት።

በውል አስተዳደር፣ በተጫዋች አስተዳደር (Player Management) እና በዝውውር ስትራቴጂ ላይ ክለቦች ተከታታይ ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ።

ክለቦች የአጭር ጊዜ ውጤት ብቻ ሳይሆን የረጅም ጊዜ የተጫዋች ልማትና የዝውውር ገቢን መሠረት ያደረገ አስተዳደር እንዲከተሉ ማድረግ።

የክለብ አመራሮች በውል አስተዳደር እና በስፖርት ቢዝነስ ላይ የሙያ ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ።

የ2 ዓመት ውል መፈረም ሕገ-ወጥ አይደለም፤ ነገር ግን በሁሉም ተጫዋቾች ላይ ይህንኑ ብቻ መጠቀም የውል አስተዳደር ድክመትን ያሳያል።

ዘመናዊ እግር ኳስ ተጫዋችን እንደ የክለብ ሀብት (Club Asset) ይመለከታል፤ ስለዚህ የውል አስተዳደር የረጅም ጊዜ የቴክኒክ፣ የኢኮኖሚ እና የውድድር እቅድ አካል መሆን አለበት። ይህን ባህል በማሻሻል የኢትዮጵያ ክለቦች በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ የተጫዋች ገበያ የተሻለ ተወዳዳሪ መሆን ይችላሉ።

🔴ፊፋ ለሠጠኝ ዕውቅናና ምስጋና የተሠጠ አፀፋዊ ምላሽ🔴ኩራትም፣ክብርም ተሠምቶኛል የእግር ኳሱን ገዥ ፊፋን ከልብ አመሠግናለሁ፤ህልሜ ዕውን እንዲሆን ከጎኔ የሆናችሁ በሙሉ ዕውቅናውም ምስጋናውም...
26/07/2026

🔴ፊፋ ለሠጠኝ ዕውቅናና ምስጋና የተሠጠ አፀፋዊ ምላሽ

🔴ኩራትም፣ክብርም ተሠምቶኛል የእግር ኳሱን ገዥ ፊፋን ከልብ አመሠግናለሁ፤ህልሜ ዕውን እንዲሆን ከጎኔ የሆናችሁ በሙሉ ዕውቅናውም ምስጋናውም የእናንተ ነውና ልትኮሩ ይገባል

Dear FIFA World Cup 2026 Media Team,

Subject: A Heartfelt Thank You

Thank you very much for your email of July 20, 2026.

Reading your message was one of the proudest and happiest moments of my professional career. To receive such recognition from FIFA, the world's highest governing body of football, is an honour that I will always cherish.

Being selected as one of the 16,000 sports journalists from around the world to cover the FIFA World Cup 2026 is a privilege beyond words.

Having the opportunity to witness the first-ever FIFA World Cup hosted by three nations, with 48 teams competing on football's biggest stage, is an experience that will remain with me for the rest of my life.

As an international sports journalist from Ethiopia, I do not take this opportunity for granted. Your trust in my work means more than I can express.

It inspires me to continue telling the stories of football with professionalism, passion, and integrity.

Please accept my sincere gratitude for the confidence you have placed in me. I also wish to thank everyone involved in making this historic tournament possible and for giving journalists like me the opportunity to be part of football history.

I sincerely hope our paths will cross again at future FIFA competitions. Until then, I will always look back on this experience with pride and gratitude.
Thank you for helping me live a dream and for giving me memories that I will carry with me throughout my life.

With my deepest appreciation,

Yishak Belay

(International Sports Journalist
Hattrick Sport Official)

🔴በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ ውድድር በሮም በልዩ ድምቀት ይጀመራል🔴ኢንስትራክተር ካሳሁን ተካ በዋና የክብር እንግድነት ይገኛል✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ...
25/07/2026

🔴በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ ውድድር በሮም በልዩ ድምቀት ይጀመራል

🔴ኢንስትራክተር ካሳሁን ተካ በዋና የክብር እንግድነት ይገኛል

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

21ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ ውድድር ነገ(ሠኞ) በጣሊያን ሮም በሳላሪያ ስፖርት ቪሌጅ በልዩ ድምቀት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

ከውድድር ባለፈ ኢትዮጵያዊያንን በአንድ መድረክ በማሠባሠብ ፍቅራቸውን፣ናፍቆታቸውን የሚወጡበት፣ስለሀገራቸው ሰብሠብ ብለው የሚመክሩበት፣አንድነታቸውን የሚያሳዩበት፣ስለ ባህላቸው፣ቋንቋቸው፣አልባሳታቸውና ስለምግባቸው ጭምር ለሌላው አለም በተግባር የሚያሳዪበት ዓመታዊ ፕሮግራማቸውን የፊታችን ሠኞ(July 27)በሳላሪያ ስፖርት ቪሌጅ በልዩ በድምቀት ለማክበር በመጨረሻው ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ታሪካዊ ክብረ በዓል ላይ ለመታደም ከመላው አውሮፓና ከሠሜን አሜሪካና ከተለያዩ ሀገራት በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ ጣሊያን ሮም መግባት ጀምረዋል።

ዓመታዊ ውድድሩን ለማድመቅና ታዳሚዎችን ዘና ፈታ ለማድረግ ተወዳጅ ድምፃዊያንም ጣሊያን ሮም መግባታቸው የተሠማ ሲሆን እንደ የፌዴሬሽኑ የመረጃ ምንጮቻችን ከሆነ ድምፃዊ ፍቅረዓዲስ ነቅዓጥበብ፣ድምፃዊ ካሳሁን እሸቱ፣ድምፃዊ ታረቀኝ ሙሉ እና ከስድስት ያላነሱ ዲጄዎች በዓሉን ልዩ ድባብ ያላብሱታል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ እግር ኳስ በተጫዋችነት፣በአሠልጣኝነት፣በኢንስትራክተርነት(በመምህርነት) እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአመራርነት በማገልገል ስሙን በወርቅ ቀለም በደማቁ ያፃፈው ኢንስትራክተር ካሣሁን ተካ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ የሠጠውን የላቀ አገልግሎት ግምት ወስጥ በመክተት የዓመታዊ ውድድሩ ዋና የክብር እንግዳ ሆኖ መጋበዙ ውድድሩን የተለየ ክብርን አጎናፅፎታል።

እግር ኳስን በትልቅ ደረጃ በጠመንጃ ያዥ ቡድን በመጫወት የኢትዮጵያን እግር ኳስ በይፋ የተቀላቀለው ኢንስትራክተር ካሣሁን ተካ በታላቁ አሠልጣኝ ሉቻኖ ቫሳሎ አይን ውስጥ በመግባቱ በወቅቱ ታላቅ በነበረው የኮተን(ጨርቃ ጨርቅ) ቡድን የመጫወት ዕድል ያገኘ ሲሆን በመቀጠልም በኢትዮጵያ እግር ኳስ የገዘፈ ስምና ውጤት ያለውን ቅዱስ ጊዮርጊስን በመቀላቀል ታሪክ የማይረሳው ድንቅ ጊዜን በሞት ከተለዩት የሙያ ጓደኞቹ አስራት ኃይሌና ስዩም አባተና ሌሎች ስመ-ጥር ተጫዋቾች ጋር ማሳለፉ ይታወሳል።

በአሠልጣኝነትም አቃቂ ጨርቃ ጨርቅ፣ቃጫ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣መብራት ኃይል፣መድን፣ኢትኮባና መድን የእሱን የስልጠና በረከት የቀመሱ ክለቦች ናቸው።

በ21ኛው በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ፌዴሬሽን ዓመታዊ በዓል ላይ እንዲገኝ በክብር የተጋበዘው ኢንስትራክተር ካሣሁን ተካ የክብር ጥሪውን አክብሮ ትናንት(ቅዳሜ)ጣሊያን ሮም መግባቱም ታውቋል።

🔴ሁሉም ሊያነበው የሚገባ🔴በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ዝውውር  የአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የግል ምልከታ(የመጀሠሪያ ክፍል)🔴በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ዝውውር ላይ የሚታዩ ኢ-ሙያዊ እና ኢ-...
25/07/2026

🔴ሁሉም ሊያነበው የሚገባ
🔴በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ዝውውር የአቶ ገዛኸኝ ወልዴ የግል ምልከታ(የመጀሠሪያ ክፍል)

🔴በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ዝውውር ላይ የሚታዩ ኢ-ሙያዊ እና ኢ-ግልጸኝነት ችግሮች ከፊፋ (FIFA) ሕግጋት አንጻር

✍️✍️በአቶ ገዛኸኝ ወልዴ(የቀድሞ የኢትዮጵያ ቡና ስራ አስኪያጅ፤በአሁን ሠዓት የኢት.ኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ዋና ፀሐፊ)በግል የቀረበ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ዕድገት ላይ ትልቅ ማነቆ እየሆነ የመጣው ዋነኛው ጉዳይ የተጫዋቾች ዝውውር ሥርዓት አልበኝነት ነው። የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (FIFA) የተጫዋቾችን ደረጃ እና ዝውውር በተመለከተ ግልጽ መመሪያዎችን (Regulations on the Status and Transfer of Players - RSTP) ቢያስቀምጥም፣ በሀገራችን ያለው አፈጻጸም ግን አሁንም ከሙያዊ አሰራር የራቀ፣ ኢ-ግልጸኝነት የበዛበት እና ከሕግ ውጪ የሚከናወን ነው።

👉ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ዝውውር ላይ የሚታዩትን ዋና ዋና ኢ-ሙያዊ ድርጊቶች እና ከፊፋ ደንቦች ጋር ያላቸውን መጣረስ በዝርዝር ይዳስሳል።

🔴1. ከፊፋ መመሪያዎች ውጪ የሚደረጉ ዝውውሮች (Breach of FIFA RSTP)
የፊፋ የዝውውር መመሪያዎች ማንኛውም ክለብ ከተጫዋች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት ተጫዋቹ አሁን ካለው ክለብ ጋር ያለውን የውል ስምምነት እንዲያከብር ያስገድዳሉ። አንድ ተጫዋች ውሉ ሊያልቅ 6 ወራት ካልቀሩት በስተቀር ሌላ ክለብ በምስጢር ማነጋገር ወይም ቅድመ-ውል መፈረም አይችልም።

🔴ያለው እውነታ፦ በኢትዮጵያ ግን ክለቦች በውል ስር ያሉ ተጫዋቾችን በምስጢር ማነጋገር፣ ገንዘብ በካሽ (በእጅ) መስጠት እና ከሕግ ውጪ ማባበል የተለመደ ተግባር ነው።
የሚፈጥረው ችግር፦ ይህ አሰራር በክለቦች መካከል ያለውን ስፖርታዊ ጨዋነት የሚያጠፋና ተጫዋቾች በሜዳ ላይ ያላቸውን ትኩረት እንዲያጡ የሚያደርግ ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊት ነው።

🔴2.የ ሕገ-ወጥ ደላሎች ጣልቃ ገብነት
ፊፋ የተጫዋቾች ወኪሎች (Agents/Intermediaries) ሕጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ እንዲኖራቸው እና በዝውውር ወቅት የሚያገኙት ኮሚሽን በግልጽ በሲስተም ውስጥ እንዲመዘገብ ያዛል።

🔴ያለው እውነታ፦ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ አብዛኞቹ ዝውውሮች የሚመሩት ፈቃድ በሌላቸው፣ የእግር ኳስ እውቀቱ በሌላቸው የጎዳና ላይ ደላሎች፣ ጓደኞች ወይም ዘመዶች ነው። ዝውውሮች የሚፈጸሙት በካፌዎችና በሆቴሎች ውስጥ በሚስጢር ነው።

🔴የሚፈጥረው ችግር፦ ደላሎች የራሳቸውን ጥቅም ብቻ በማስቀደም ተጫዋቾችን ከአንድ ክለብ ወደ ሌላ ክለብ ያላግባብ ያዘዋውራሉ። ይህም ተጫዋቾች የተሻለ የሙያ ዕድል እንዳያገኙና ሕጋዊ ጥበቃ እንዳይኖራቸው ያደርጋል።

🔴3. ሁለት ውል መፈረም (Dual Contracts) እና የግብር ማጭበርበር
በፊፋ ሕግ መሰረት አንድ ተጫዋች ለአንድ የውድድር ዘመን ሊኖረው የሚችለው አንድ ሕጋዊ ውል ብቻ ነው። ውሉ በፊፋ የዝውውር ሥርዓት (⁠FIFA TMS) ወይም በሀገር ውስጥ ዲጂታል ሲስተም መመዝገብ አለበት።

🔴ያለው እውነታ፦ በኢትዮጵያ በርካታ ክለቦች እና ተጫዋቾች ሁለት ውል ይፈራረማሉ። አንደኛው ዝቅተኛ ክፍያ የሚያሳይ ሆኖ ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ለግብር ሠብሳቢ መስሪያ ቤት የሚቀርብ ሲሆን፣ ሁለተኛው እና ትክክለኛው ከፍተኛ ክፍያ የያዘው ውል ግን በሚስጥር ይያዛል።

🔴የሚፈጥረው ችግር፦ ይህ ፍጹም ሕገ-ወጥ እና ኢ-ሙያዊ አሰራር ነው። በክለብ እና በተጫዋች መካከል አለመግባባት ሲፈጠር ፌዴሬሽኑ የሚቀበለው ዋናውን (ለእነሱ የቀረበውን ዝቅተኛ ውል) በመሆኑ ተጫዋቾች መብታቸውን ያጣሉ። በተጨማሪም የሀገርን የግብር ሥርዓት የሚያጭበረብር ተግባር ነው።

🔴4. በዲጂታል የዝውውር ሥርዓት (TMS) አለመመራት
ፊፋ ዓለም አቀፍ የዝውውር የዲጅታል ሥርዓትን (Transfer Matching System - TMS) ያስገደደ ሲሆን፣ አሁን ላይ የሀገር ውስጥ ዝውውሮችም (Domestic TMS) በዲጂታል መንገድ እንዲመዘገቡ ይፈልጋል።

🔴ያለው እውነታ፦ በኢትዮጵያ የዲጂታል አሰራር ደካማ በመሆኑ ዝውውሮች አሁንም በወረቀት እና በአካል በመገኘት ይከናወናሉ። ይህም ሰነዶች እንዲጠፉ፣ የውል ዘመን እንዲጭበረበር እና የተጫዋቾች ትክክለኛ ዕድሜና ታሪክ እንዳይታወቅ በር ይከፍታል።
የሚፈጥረው ችግር፦ የተጫዋቾች መረጃ በአግባቡ ባለመያዙ ሀገሪቱ ከተጫዋቾች ሽያጭ ማግኘት የሚገባትን የኮምፔንሴሽን (Training Compensation) ክፍያ ታጣለች አሁን ባው ሁኔታ በዓለም አቀፍ ዝውውር ውስጥ ተሳታፊ ባንሆንም ይህ ባለመሆኑ ግን ክለቦች ተጫዋቾችን በነፃ እንዲለቁ ይገደዳሉ።

🔴5. የውል ግዴታዎችን አለማክበር እና የደሞዝ መዘግየት
ፊፋ ተጫዋቾች ደሞዛቸው ከሁለት ወር በላይ ካልተከፈላቸው ውላቸውን በፍትሐዊ ምክንያት (Just Cause) አቋርጠው በነፃ የመልቀቅ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።

🔴ያለው እውነታ፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ለተጫዋቾች ለወራት ደሞዝ አለመክፈል የተለመደ ነው። ተጫዋቾች መብታቸውን ሲጠይቁ ከቡድን እንዲገለሉ ይደረጋል ወይም ማስፈራራት ይፈፀምባቸዋል ። በሌላ በኩል ተጫዋቾችም አላግባብ ልምምድ በማቋረጥ ኢ- ሙያዊ ስነምግባር ይፈፅማሉ።
የሚፈጥረው ችግር፦ ይህ ድርጊት የእግር ኳሱን የኢኮኖሚ ዋስትና የሚያናጋ ሲሆን፣ ተጫዋቾች በስነ-ልቦና ተጎድተው ብቃታቸው እንዲቀንስ ያደርጋል።

🔴6. የቅድመ-ውል ስምምነት (Pre-contract agreement) ከፈረሙ በኋላ፣ ስምምነቱን ለፈረሙበት ክለብ ሳያሳውቁና ውሉን በድንገት ችላ በማለት (ignored) ከሌላ ክለብ ጋር ደርበው መፈረም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ የሚታይ እጅግ ከባድ ሕገ-ወጥ እና ኢ-ስነምግባራዊ ድርጊት ነው።ይህ ድርጊት ከዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (FIFA) የተጫዋቾች ደረጃ እና ዝውውር መመሪያ (Regulations on the Status and Transfer of Players - RSTP) አንጻር እንዴት እንደሚታይ እና በስፖርቱ ላይ የሚያመጣው አደጋ ስንመለከት

🔴 የፊፋ (FIFA RSTP) ሕጋዊ ድንጋጌ ምን ይላል?በፊፋ ሕግ አንቀጽ 13 እና 18 (RSTP Articles 13 & 18) መሰረት፣ በክለብ እና በተጫዋች መካከል የሚደረግ ማንኛውም ውል ሊከበር ይገባል አንድ ተጫዋች አሁን ካለው ክለብ ጋር ያለው ውል ሊያልቅ 6 ወር ወይም ከዚያ በታች ሲቀረው፣ ከሌላ አዲስ ክለብ ጋር ሕጋዊ የቅድመ-ውል ስምምነት መፈረም ሙሉ መብቱ ነው።ይህ የቅድመ-ውል ስምምነት ልክ እንደ መደበኛ ውል ሕጋዊ አስገዳጅነት አለው። ተጫዋቹ ውሉን ያለምንም በቂ ምክንያት (Without Just Cause) ማቋረጥ ወይም ችላ ማለት አይችልም።ይህንን ሕግ በመጣስ የቅድመ-ውል ፈርመው እያለ በድብቅ ወደ ሌላ ክለብ የሚሄዱ ተጫዋቾች እና ይህንን የሚያደርጉ ክለቦች የሚከተሉትን ከባድ ጥፋቶች እንደፈጸሙ ይቆጠራል፦

🔴የውል ታማኝነትን ማጥፋት (Breach of Contract)፦ ተጫዋቾች ቅድመ-ውል ከፈረሙ በኋላ የተሻለ የገንዘብ ክፍያ ሲያዩ ብቻ የመጀመሪያውን ክለብ ዝም ብለው ችላ ማለታቸው ሙያዊ ጨዋነት የሌላቸው (Unprofessional) መሆናቸውን ያሳያል። ውልን እንደ ተራ ወረቀት መቁጠር የስፖርቱን የሕግ የበላይነት ያጠፋል።ድርብ ምዝገባ እና ማጭበርበር (Dual Registration Intent)፦ ለአንድ የውድድር ዘመን ከሁለት ክለቦች ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ስምምነት መፍጠር ፍጹም ሕገ-ወጥ ነው። ይህም ተጫዋቾች ለገንዘብ ብቻ ሲሉ የስፖርታዊ ጨዋነትን (Fair Play) መርህ እየጣሱ መሆናቸውን ያሳያል።

🔴 ሁለተኛው ተጫዋቹን ያስፈረመው ክለብ፣ ተጫዋቹ ቀደም ሲል ቅድመ-ውል መፈረሙን እያወቀ ወይም ሳያጣራ ውል እንዲያፈርስ ካደረገ፣ በፊፋ ሕግ መሰረት ተጫዋቹ ውል እንዲያፈርስ ያባበለ/የገፋፋ ተብሎ በከባድ ጥፋተኝነት ይጠየቃል።

🔴በፊፋ ሕግ ተጫዋቹ መጀመሪያ ውል ከፈረመበት ክለብ እውቅና ውጪ ሌላ ቦታ ሄዶ ሲፈርም፣ የመጀመሪያው ክለብ ቅሬታውን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ወይም ለፊፋ ካቀረበ የሚከተሉት ቅጣቶች ይከተላሉ፦ስፖርታዊ ቅጣት በተጫዋቹ ላይ (Sporting Sanctions)፦ ተጫዋቹ ያለምንም በቂ ምክንያት ውል በማፍረሱ ምክንያት ከ4 እስከ 6 ወራት ከማንኛውም ይፋዊ ጨዋታ ይታገዳል።ተጫዋቹ እና ሁለተኛው ያስፈረመው ክለብ በጋራ በመሆን መጀመሪያ ቅድመ-ውል ለፈረመው ክለብ የጉዳት ካሳ (Compensation) እንዲከፍሉ ይገደዳሉ።በሁለተኛው ክለብ ላይ የሚጣል ቅጣት፦ ተጫዋቹ ውል እንዳለው እያወቀ ያስፈረመው ሁለተኛው ክለብ ለአንድ ወይም ለሁለት የዝውውር መስኮት አዲስ ተጫዋች እንዳያስፈርም (Transfer Ban) ይታገዳል::

👉ማጠቃለያ እና የመፍትሔ ሐሳቦች በሁለተኛ ክፍል ይቀርባል::
(...ይቀጥላል....)

🔴ጋዜጠኛ ኃይለእግዚአብሄር አድኃኖም በታሪካዊው ውድድር ላይ ስለነበረን ጊዜ ከልብ አመሠግናለሁ 🙏🙏በአሜሪካ በተካሄደው ታሪካዊ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ከጋዜጠኛ ኃይለእግዚአብሄር አድኻኖም ጋር ያ...
22/07/2026

🔴ጋዜጠኛ ኃይለእግዚአብሄር አድኃኖም በታሪካዊው ውድድር ላይ ስለነበረን ጊዜ ከልብ አመሠግናለሁ 🙏🙏

በአሜሪካ በተካሄደው ታሪካዊ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ከጋዜጠኛ ኃይለእግዚአብሄር አድኻኖም ጋር ያሳለፍኩት ጊዜ በሕይወቴ የማይረሳ ትዝታ ሆኖ ይቀራል፤ይህን ልዩ አጋጣሚ ከሙያ አጋሬ እና ከቅን ወዳጄ ኃይሌ ጋር በመካፈሌም ከፍተኛ ደስታና ኩራት ተሰምቶኛል።

ኃይልዬ ቀናነትህ፣ ለሰዎች ያለህ አሳቢነት፣ ተቆርቋሪነትና ድጋፍ ከቃላት በላይ ነው፤ውድድሩን አብረን ከመከታተል አልፈን ኒውዮርክን አብረን እስከ መጎብኘት ድረስ፣ በጉዞው ሁሉ ምቾት እንዲሰማኝና ምንም እንዳይጎድልብኝ በትዕግሥትና በፍቅር ከጎኔ ቆመሃል፤ለዚህም የማመስገኛ ቃላት አጥረውኛል።

ከአንተ ጋር በሁለት የአቴሌቲክስ ሻምፒዮናዎች በአሜሪካ ዩጂን ኦሪገን እና በሀንጋሪ ቡዳፔስት አሁን ደግሞ በአሜሪካ ኒውጀርሲ የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ያሳለፍነው ጊዜ ቅንነትህን፣ ደግነትህን፣ ሰውን በክብርና በፍቅር የመያዝን መልካሙን ልብህን ይበልጥ እንዳይ ከማድረጉም በላይ አስተምሮኛል።

ከአንተ ጋር ያሳለፍኳቸው የሙያ ቆዬታዬና ጉዞዎቼ ሁሉ ለሕይወቴ ትልቅ ትርፍ ያበረከቱ ናቸው፤የማይረሱ ትዝታዎችም ሆነው ለዘላለም ከእኔ ጋር አብረው ይኖራሉ።

በመጨረሻም: ይህን ታሪካዊ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ አብረን እንድናሳልፍ ስለፈቀድክልኝ፣ እንዲሁም በባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ሊመዘን ለሚችለው እንክብካቤህ፣ ፍቅርህና ከልብ ለሰው የምትሰጠው ክብር ኃይልዬ ከልብ አመሰግንሃለሁ።
እግዚአብሔር ጤና፣ ረጅም ዕድሜ፣ በረከትና በሙያህ ከአሁኑ የበለጠ የላቀ ስኬት እንድታስመዘግብ ከልብ እመኛለሁ፤
ከልቤም አመሰግንሃለሁ።

✍️✍️የጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ የ2026 የፊፋ የአለም ዋንጫ ፍፃሜ የጉዞ ማስታወሻ(ክፍል 1)🔴ከፈተና በኋላ የተገኘ ደስታ፣ ከጭንቀት በኋላ የተሰጠ ሽልማት፣ እና በውጣ ውረዶች የተጻፈ የማይረ...
22/07/2026

✍️✍️የጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ የ2026 የፊፋ የአለም ዋንጫ ፍፃሜ የጉዞ ማስታወሻ(ክፍል 1)

🔴ከፈተና በኋላ የተገኘ ደስታ፣ ከጭንቀት በኋላ የተሰጠ ሽልማት፣ እና በውጣ ውረዶች የተጻፈ የማይረሳ ታሪክ

📌እንደ መንደርደሪያ

የ2026 የአለም ዋንጫ አርጀኔቲናን 1ለ0 ያሸነፈችውን ስፔንን ሻምፒዮን አድርጎ የመጨረሻው ፊሽካ ተነፍቶ ቢጠናቀቅም፣ በዚህ ረጅሙ የአለም ዋንጫ ጉዞ ያሳለፍኩት ታሪክ ግን ገና አልተጠናቀቀም፤አሁንም በአእምሮዬ በግልጽ ታትሞ ተቀምጧል፤

የአለም ዋንጫን ለመዘገብ ያደረኩት ጉዞ በደስታና በስኬት ብቻ የተሞላ አልነበረም፤ ብዙ ያልተጠበቁ ፈተናዎች በጉዞዬ ገጥመውኛል፤ በተለይም በፍፃሜው ዕለት ያሳለፍኩት ውጣ ውረድ ከእስከዛሬዎቹ ሁሉ የማልረሳው ተሞክሮ ነው፤ በብዙ ፈተናዎች መካከል ተቋቁሜ በዚያ ታሪካዊ የፍፃሜ ጨወታ ዕለት መገኘቴ ለእኔ ከሙያ ስኬት በላይ የሕይወት ትምህርት ሆኖልኛል፤

ከዛሬ ጀምሮ ይህን የጉዞ ማስታወሻዬን በተከታታይ ክፍሎች አጋራችዋለሁ፤ከመነሻው እስከ ፍፃሜው ቀን ድረስ ያጋጠሙኝን ፈተናዎች፣ ያልተጠበቁ አጋጣሚዎች፣ የደስታና የጭንቀት ቅጽበቶች፣ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ክስተት የተማርኩትን፣በተለይ ከሜዳ ውጪ ያሉትን በተከታታይ ለእናንተ አካፍላለሁ፤
አብራችሁኝ ቆዩ፤ ይህ የአለም ዋንጫ የጉዞ ማስታወሻዬ በሜዳ ላይ ስለነበረው ኹነት ብቻ ሳይሆን፣ ወደዚያ ለመድረስ ስለተጓዝኩበት ጉዞም ጭምር የሚተርክ ነው፤ተከታተሉኝ።

🔴ፈተናና መሰናክል (1)

አንዳንድ ጉዞዎች በእግር ሳይሆን በልብ ይጀምራሉ፤የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ በመገኘት ህያው ምስክር ለመሆንና ሌላ አዲስ ታሪክ የማፃፍ ዕቅድን ይዤ ወደ ኒው ጀርሲ ስታዲየም የጀመርኩት ጉዞም እንዲሁ በዚሁ ስሜት የታጀበ ነበር።

የዓለም ዋንጫ ፍፃሜን ለመዘገብ ወደዚያ እያመራሁ የነበረው እንደ ማንኛውም ተመልካች ጨዋታ ለማየት ብቻ አልነበረም፤ እንደ ስፖርት ጋዜጠኛ በሙያዬ የተለየ ስፍራ ያለውን ህልሜን ለማሳካት እንጂ።

ከዚህ ቀደም በሁለት የዓለም ዋንጫ ፍጻሜዎች ተገኝቼ ዘግቤያለሁ፤ይህ ግን ሦስተኛ የአለም ዋንጫ ተሳትፎዬ ሆኖ እንዲመዘገብ ወደ ታሪክ እየተንደረደርኩ ነው፤እሁድ ጁን 19/5026 ለእኔ ልዩና ምንአልባትም ታሪካዊ ቀኔ ነበረች፤ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በዘለቀ ጥረት የገነባሁትን የሙያ ጉዞ የሚያሳካ፣በሕይወቴም የማይረሳ ታሪካዊ ቀን።

🔴ፍርሃት፣የመረበሽ ስሜት፣ሰጋት(2)

ያ ታሪካዊ ይሆናል ያልኩት ቀን ከወትሮ በተለየ አንዳች ባዕድ የሆነ ስሜትም እንዲሠማኝ ያደርግ ነበር፤ታሪክ ለማፃፍ፣ ጉጉቴን የሚበልጥ ያልታወቀ የጭንቀት፣የመረበሽ ስሜት ውስጤን አጥለቅልቆታል።

ምክንያቱን ባላውቀውም፣ ልቤ እንደማስጠንቀቂያ ደወል የፍርሃት ደውል ደጋግሞ ያለማቋረጥ ይመታ ነበር።

🔴138 ዶላሬና የገጠመኝ ፈተናና ጭንቀቴ(3)

ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኒው ጀርሲ የሚወስደኝን የFlixBus ትኬት 138 ዶላር ከፍዬ ከህልሜ ለመድረስ
ኢንስትራክተር ካሳሁን ተካ በፍቅር፣በእንክብካቤ እንቅልፉን ሠውቶ፣አብልቶ አጠጥቶ እስከ ዩኒየን ስቴሽን አደረሰኝ፤

ነገር ግን በውስጤ ያለው መረበሽ ከመቀነስ ይልቅ ስለበረታ፣ጭንቀቱና የመረበሽ ስሜቱ አእምሮዬን በመቆጣጠሩ በአግባቡ እንኳን ሳልሰናበተው ከመኪናው ወርጄ ወደ ጣቢያው ሮጥኩ።

ወደ ጣቢያው(Station)እንደገባሁ የመጀመሪያው ፈተና ጠበቀኝ፤ረጅም ሰልፍ ነበር፤ገና በማለዳ ረዥሙን ሠልፍ ሳየው አደከመኝ፤በዚህ መሃል ከፊቴ የቆመውን አንድ አሜሪካዊ "ይህ ወደ ኒው ጀርሲ የሚሄደው ነው?" ብዬ ስጠይቀው አንገቱን ጭምር በመነቅነቅ"አዎ፣ በትክክለኛ ቦታ ላይ ነህ" አለኝ።

በለበስኩት የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለበት ጀግኖች አትሌቶቻችን የሚለብሱት የአሸናፊነት ምልክት ተደርጓ በሚወሠደው ቱታ መደነቁን አይንቹና ፊቱ እያሳበቁበት ብዙም ሳይቆይ "ከየት ነህ?" የሚል በጣም የማልወደው ቀፋፊ ጥያቄ ጠየቀኝ፤ንዴቴን ዋጥ አድርጌ ከኢትዮጵያ ብዬ መለስኩለት፤እሱ ግን በዚህ አላበቃም አስከተለና "ትኬትህን በስንት ገዛኸው?በጣም ተወዷል አይደል " ሲል ጠየቀኝ።

"አዎ በጣም ተወዷል፤እኔ ግን ትኬት አልገዛም፣በትኬትም አልገባም፤ ከ16 ሺህ በላይ ከመላው ዓለም ከተመረጡ ጋዜጠኞች አንዱ ሆኜ በሚዲያ ባጄ ነው የምገባው ብዬ ደረቴ ላይ ያለውን ባጄን አሳየሁት፣ በመደነቅ ስሜት ቃና ያለው በሚመስል ድምፅ "ዋው! በጣም ዕድለኛ ነህ" አለኝ፤ይሄን ሁሉ እሱ ሲጠይቅና እኔ ስመልስ የነበረው ከቀልቤ ነበር ለማለት ይቸግረኛል፤ቀልቤ አብሮኝ አልነበረም፤

ምክንያቱን በማላውቀው ነገር አእምሮዬ አንዳች መግኒጥሳዊ ኃይል ተቆጣጥሮታል፤ከመረበሼና የስጋቴ መጠን በድንገት እንደ ዶላር ዋጋ ከፍ በማለቱ ለሁለተኛ ጊዜ "እርግጠኛ ነህ?ይሄ ወደ ኒውጀርሲ ስታዲየም ነው?" ብዬ ስጠይቀው ሳቅ በተሞላበትና ፌዝ በሚመስል መልኩ "አታስብ በጣም በትክክለኛ ቦታ ላይ ነህ" አለኝ።

ቃሉን አምኜ ወደ ውስጥ ገባሁ፤ውስጥ ስገባ ግን ከፊቴ የቆመው አውቶቡስ ሳይሆን ባቡር ነበር።
ዞር ብዬ ሰውየውን ፈለግሁት፤ ግን ጠፍቷል፤አረ እንደውም በቅፅበት ተሠውሮብኛል፤ያኔ አንድ ነገር እንዳለ ወይም እንደተሳሳትኩ ገባኝ። በ"FlixBus ነው የምሄደው የት ነው ባሱን የማገአው?" ብዬ ስጠይቅ "እዚህ አይደለም ከላይ ነው፤ በፍጥነት ሂድ!" አሉኝ።

🔴ለሪከርድ እንደሚሮጥ አትሌት ወደ አውቶብስ ሩጫ (4)

ሰዓቴን እያየሁ ለሪከርድ እንደሚሮጥ አትሌት በዛ ሠውነቴ ሮጥኩ፤ ኤስካሌተሩን ወጥቼ የአውቶብስ መሳፈሪያው ጋ ደርሼ ሠዓቴን ሳይ የሰዓት መቆጠሪያው 6፡04 ይላል፤ አውቶቡሱ በ6፡00 ተነስቶ ሄዷል፤አራት ደቂቃ ነገሮቼን፣ታሪኮቼን የማበላሸት እርምጃ ውስጥ እንደገቡና አለም ሁሉ በጉጉት ከሚጠብቀው ታሪካዊ የፍፃሜ ጨዋታ ውጭ ሊያደርገኝ እንደነበር ተሠማኝ፤ፈረንጆች ለጊዜ ያላቸውን ዋጋ እንኳን በዚህ ደረጃ ተቀጥቼ ይቅርና ቀድሜም አውቅ ስለነበር በአራት ደቂቃማ ህልሜ አይገታም ብዬ ወደ ሁለተኛ አማራጭ ገባሁ፤

🔴የአራት ደቂቃ ዋጋው ስንት ነው?(4)

እጅግ ውድ ነው፤ይህንን ደግሞ አትሌቶች ለማይክሮ ሰከንድ የሚሠጡትን ዋጋ በቅርቡ ስለማውቅ አራት ደቂቃ ዋጋዋ እጅግ ከፍ ያለ እንደሆነ ለመረዳት ምርምር አይጠይቅም፤ትንሽ የምትመስለው አራት ደቂቃ ጉልበት ኖሯት የወራት ዝግጅቴን እና የዓመታት ህልሜን ለማፍረስ ተቃርባ ነበር፤ዩኒዮን ስቴሽን ውስጥ ወደሚገኘው ትኬት ቢሮ ሄጄ ሁኔታውን ለትኬት ኦፊሠሯ ስገልጽ እሷም "በጣም አዝናለሁ፤ አውቶቡሱ ሄዷል" አለችኝ፤በምላሿ ውስጤ ተሠበረ፤የተሰበረው 138 ዶላር የከፈልኩበት የማለዳ ጉዞዬ ብቻ አልነበረም፤ የሦስተኛ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜን በቦታው ተገኝቼ የመዘገብ ህልሜም እንጂ።

ሆኖም በዚያ ቅጽበት ልቤና አእምሮዬ አንድ ነገር ተስማሙ፤ "ይህ ጉዞ በአራት ደቂቃ አያበቃም፤የሦስተኛ የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ ጨዋታን ሳልዘግብ፣በሙያዬ አዲስ ታሪክ ሳላፅፍና ህያው ምስክር ሳልሆን አልመለስም ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ።

🔴የአውቶብስ ትኬት ስለመወደዱና በየሠከንዱ መሸጡ(Sold out)(5)

ወደ መዳረሻዬ ለመድረስ የያዝኩት የመጀመሪያው FlixBus አመለጠኝ፤ያን ጊዜ የተሰማኝ ብስጭት በቀላሉ የሚገለጽ አልነበረም፤ትኬቴ እንደማይመለስ ሲነገረኝ 138 ዶላር ከእጄ እንደወጣ ተሰማኝ፤ በተለይም ዶላር ለመቆጠብ የሚታገልና ዋጋዋን ጠንቅቆ ከሚረዳ ሀገር ለመጣ ሰው ያ ኪሳራ ከገንዘብ በላይም የህልም መደናቀፍ መስሎ ተሠማኝ።

“መፍትሄው ምንድነው?” ብዬ ስጠይቅ አዲስ ትኬት መቁረጥ እንዳለብኝ ተነገረኝ፤ሪፈንድ(ተመላሽ) እንዲደረግልኝ ስጠይቅም “የተቋሙ ፖሊሲ ነው፤አይመለስም” የሚል ድፍን ያለ መልስ ብቻ አገኘሁ፤በዚያ ቅጽበት ብስጭቴና ጭንቀቴ ተቀላቀሉ፤ቀጣዩን አማራጭ ስፈልግ ዋጋው በፍጥነት ጨምሮ ነበር፤ከትኬት ኦፊሰሯ ጋር እየተከታተልኩ ሳለሁ በ183 ዶላር አንድ ቦታ እንዳለና ትኬት እየተወደደና Sold Out (ተሸጦ እያለቀ)በመሆኑ መፍጠን እንዳለብኝ ነገረችኝ።

ለመወሰን ጥቂት ጊዜ ወሰድኩ፤ ስመለስ ግን ያ እድልም ጠፍቶ ጠብቀኝ ፤እንደተፈራው “Sold out ሆኗል” የሚለውን ቃል በዚያ ቅጽበት ስሠማ ሌላ ከባድ ጫና ሆኖብኝ ፤
በዚያ ሁኔታ ቆሜ “ምንድነው የሚከታተለኝ?” ብዬ ራሴን እስከመጠየቅ ሁሉ ደረስኩ፤ የሚቀጥለው ጉዞ 9፡30 እንደሆነ ሲነገረኝ ደግሞ ሌላ ጭንቀት መጣ፤ ጉዞው አምስት ሰዓት የሚፈጅ በመሆኑ ለጨዋታው የመድረስ እድሌ አስፈሪ ሆነ፤
በዚያ ጊዜ አንገቴን ወደ ላይ ቀና አድርጌ ከፈጣሪዬ እርዳታ ተማፀንኩ፤በባቡርና በአውሮፕላን ብሎም በኡቨር ጭምር ለመጓዝ ስጠይቅ ዋጋቸው ክፉኛ ወደላይ ተስፈንጥሯል፤ባቡር ከ300-500 ዶላር፣አውሮፔላን እስከ 700 እና ከዚያ በላይ ኡበር እስከ 400usd መጠየቃቸው ነገሮችን ይበልጥ አወሳሰቡት ልክፈል ብልም ከኪሴ ጋር የሚመጣጠንም አዬደለም፤

በዚህ የተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ ወድቄ እየተሠቃየሁ ባለሁበት ሠዓት የእኔን ጭንቀትና ጋዜጠኛነቴን የተረዳ ሌላ የትኬት ኦፊሰር 8፡30 ላይ የሚያደርሰኝ ፈጣን የአውቶብስ አማራጭ እንዳገኘልኝ ነገረኝ፤ መጀመሪያ ከገጠመኝ ችግር በመነሳት ሁለቴ እንኳን ሳላስብና ሳላመንታ ዶላሬን መዥርጬ ከፈልኩ፤ ግን የሁለት ዓመት ያህል የረዘመ ሁለት ሰዓታትን በጭንቀት የመጠበቅ ግዴታም ወደቀብኝ

🔴ጉዞ ወደ Brooklyn 38th st እና ወደ ፔን ስቴሽን(5)

የሁለት ዓመት ያህል የረዘመው የሁለት ሰዓት ቆይታ ወይም ጥበቃ መድረሱ አይቀርም ደረሠ፤በመጨረሻ አውቶብሱ እንደ ነፋስ በሮ Brooklyn 38th st ደረሠ በመቀጠል ወደ ኒውጀርሲ ፔን ስቴሽን ሠተት ብዬ ገባሁ፤ወደ ስታዲየሙ የሚያመለክቱ ምልክቶችን በቮሎንተርሶች እጅ ሳይ የተሰማኝ እፎይታ ልዩ ነበር፤ከፔን ስቴሽን የያዝኩት ባቡር ከአንድ ስቶፕ ከተጓዝን በኋላ Secaucus Junction ስቴሽን ስንደርስ ትራንዚት በማድረግ በሌላ ባቡር ተሳፍሬ ወደ መጨረሻው መድረሻዬ ኒውጀርሲ ሴታዲየም ደረስኩ፤በስታዲየሙ በር ላይ ቆሜ የተሠማኝን ስሜት ለመግለጽ ቃላት ያንሠኛል፤ ግን በአንድ ነገር ላይ በጣም እርግጠኛ ሆንኩ፤የዘመናት ህልሜ በእጄ እንደገባ ተሰማኝ፤ከዚህ በላይ የማይረሳው ደግሞ በተገኘሁበት በዚያው ስታዲየም እኔና የዓለማችን አወዛጋቢው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በአንድ መድረክ ላይ ያንን ታላቅ የእግር ኳስ ታሪክ በመመልከት ፈተናዎቼንና ብስጭቶቼን በደስታ ቀየረልኝ።

የአውቶብስ ማምለጥ፣የትኬት መጥፋትና ዋጋ መናር፣ ከብዙ ጭንቀትና ከፍርሃት በኋላ የደረስኩበት ያ ቦታ ለእኔ የድል ስፍራ ሆነ፤ያ ቀን በህይወቴ ውስጥ የማይረሳ ታሪክ ሆኖ ተመዘገበ።

ለአንድ ሰው ቀላል የሚመስለው ጉዞ ለሌላ ሰው የህይወት ትልቅ ትዝታ ሊሆን ይችላል፤የእኔም ያ ጉዞ እንደዚህ ነበር፤ ከፈተና በኋላ የተገኘ ደስታ፣ ከጭንቀት በኋላ የተሰጠ ሽልማት፣ እና በህልም የተጻፈ የማይረሳ ታሪክ።
...(ይቀጥላል)....

📌በመጨረሻ:-

ከዛሬ ጀምሮ ይሄንን የጉዞ ማስታወሻዬን በተከታታይ ክፍሎች አጋራችዋለሁ፤ከመነሻው እስከ ፍፃሜው ቀን ድረስ ያጋጠሙኝን ፈተናዎች፣ ያልተጠበቁ አጋጣሚዎች፣ የደስታና የጭንቀት ቅጽበቶች፣ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ክስተት የተማርኩትን፣በተለይ ከሜዳ ውጪ ያሉትን አዳዲስ የዓለም ዋንጫ ክስተቶችን በተከታታይ ለእናንተ አካፍላለሁ፤መልካም ቆዬታ

🙏🙏ታላቅ ምስጋና:ይህ የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት የትራንስፖርትና የሆቴል ወጪን በመሸፈን በሠው ሀገር ባይተዋር እንዳልሆን ስልክ እየየደወለ የሚያበረታታኝ፣ቃሉን ጠብቆ ያገዘኝን ወደ ዳላስ እንድመጣም ግብዣ ያደረገልኝን በዳላስ ነዋሪ የሆነው ደጉን፣ቀናውንና ቸሩን የቀድሞ ወዳጄን አሠፋ ከበደን የፍፃሜ ጨዋታው አጋር በመሆኑ በተከበሩ አንባቢዎቼ ስም ለማመስገን እወዳለሁ፤ያለ እሱ ድጋፍ ይሄን ፈተና ለመወጣት እጅግ ይቸግረኝ ነበርና አሴ ወንድሜን ከነመላ ቤተሠቦቹ ከልብ አመሠግናለሁ።🙏🙏

21/07/2026

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911478296

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቤስት ስፖርት ኢትዮጵያ / Best Sport Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category