09/08/2022
ጎንቻሎ ጉዴስ በ30 ሚሊየን ዩሮ ዎልቭስን በቋሚ ኮንትራት ተቀላቅሏል ሲል የተጫዋቹ ክለብ ቫሌንሲያ በይፋዊ መግለጫው አረጋግጧል። 🚨🟠🇵🇹
ጉዴስ የሕክምና ምርመራውን አጠናቅቆ በቅርቡ ውሉን ይፈርማል።
ምንጭ ፦ Fabrizio Romano
አልካንትራ በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጫዋች ቲያጎ አልካንታራ ባጋጠመው ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ይፋ ተደርጓል ።
ሊቨርፑል የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታ ከፉልሀም ጋር ባደረጉበት መርሐ ግብር የጡንቻ መሸማቀቅ ያጋጠመው አልካንታራ ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ የሚርቅ ይሆናል ።
ቲያጎ አልካንታራ እስከ መስከረም አጋማሽ ለክለቡ ግላጋሎት የማይሰጥ ሲሆን ከ ክሪስታል ፓላስ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ፣ በርንማውዝ ፣ ኒውካስትል ፣ ኤቨርተን እና ዎልቭስ ጋር የሚደረጉ ጨዋታዎች ያመልጡታል ።
ዴስትኒ ኡዶጊ ወደ ቶተንሃም 𝙝𝙚𝙧𝙚 𝙬𝙚 𝙜𝙤 !
ቶተንሃም ኡዶጊን ለማስፈረም ከዩዲኔዝ ጋር ሙሉ ስምምነት ተደርሷል።
የለንደኑ ክለብ ለተጫዋቹ ዝውውር 20 ሚሊየን ዩሮ ይከፍላል። ከተጫዋቹ ጋር ከግል ስምምነቶች በኋላ ባለተሰጥኦው ጣሊያናዊ የግራ ተመላላሽ በ2023 የስፐርስ ተጫዋች ይሆናል።
እስከዛ ድረስ በአንድ አመት የውሰት ውል እዛው ዩዲኒዜ ይቆያል።
ምንጭ ፦ Fabrizio Romano
OFFICIAL ፦ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትዱ ግብ ጠባቂ ሰርጅዮ ሮሜሮ በነፃ ዝውውር የአርጀንቲናውን ክለብ ቦካ ጁንየርስ በአንድ ዓመት ኮንትራት መቀላቀሉ ይፋ ሆኗል።
ምንጭ ፦ Fabrizio Romano
ማንቸስተር ዩናይትዶች ከአድሪያን ራቢዮት እና ከእናቱ ቬሮኒኬ ጋር በቀጥታ ተገናኝተዋል!
በግል ውል ላይ ለመደራደር ከጁቬንቱስ ጋር ምንም ችግር የለም በዚህ ክረምት ራቢዮትን መሸጥ ይፈልጋሉ።
ኤሪክ ቴን ሃግ ከፈረንሳዩ ተጫዋች ጋር በተደረገው ቀጥተኛ ውይይትም ተሳትፏል።
ቼልሲዎች ለዌስሊ ፎፋና አዲስ ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ላይ ናቸው!
እና ባለፈው ሳምንት የ£70m ጥያቄ ውድቅ ከተደረገባቸው በኋላ እንደገና ሙከራ ያደርጋሉ።
➪ FabrizioRomano
ኤሪክ ቴን ሃግ ማርኮ አርናውቶቪችን ይፈልጋል እና ከእሱ አንድ ነገር ማግኘት እንደሚችል ያስባል።
ቴን ሃግ በማንቸስተር ዩናይትድ የሚፈልገውን ሁሉ እያገኘ ነው - አድሪያን ራቢኦትንም ይፈልጋል።
🚨| በርናርዶ ሲልቫ ባርሴሎናን ለመቀላቀል ደመወዙን በብዙ ዝቅ ለማድረግ ፈቃደኛ ነው።
🚨| ባርሴሎና ፍሬንኪ ዲዮንግ ቢቆይም እንኳ ለበርናርዶ ሲልቫ እንደሚፈርም ነግረውታል።
ኮስቲች ወደ ጁቬንቱስ፣ Here We Go!
ሙሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል። ክፍያ ወደ €16m ተጨማሪ ክፍያ ተካትቷል - ኮስቲች የህክምና ምርመራዎችን ለማድረግ በቅርቡ ወደ ቱሪን ይበራል።
ምንጭ፦ Fabrizio Romano
ጁቬንቱሶች ለሜምፊስ ዴፓይ የ 2 ዓመት ኮንትራት ሊያቀርቡለት ተዘጋጀተዋል ።
ምንጭ፦ Dimarzio
የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል ከታች ያለዉን ሊንክ ይጫኑ
👇
https://t.me/hulusporthighlight